ዩናይትድ ስቴትስ - የአሜሪካ ድምፅ
ዩናይትድ ስቴትስ - የአሜሪካ ድምፅ
ሁለተኛው ክትባት እየወጣ በአሜሪካና በእንግሊዝም ወረርሽኙ እየበዛ ነው
በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የገና በዓል ከመድረሱ በፊት፣ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ሁለተኛው ክትባት በስርጭት ላይ ለመዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ብርታኒያ ደግሞ አዲስ መልክ ይዞ በከፍተኛ መጠን እየተሰስፋፋ ያለውን ቫይረስ በመስጋት እንደገና ብዙ ነገሮችን ወደ መዘጋጋት እየተመለሱ ነው።
በዩናይትድ ስቴትስ፣ ባዮቴክ በተባለው የመድሃኒት አምራች ሞደርና፣ የተመረተው የኮረና ቫይረስ ክትባት፣ በዚህ ሳምንት፣ በመላው አሜሪካ ስርጭት ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይሁን እንጂ፣ ወረርሽኙን የሚከተታሉት ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ስርጭቱ የሚመጣው፣ አገሪቱ በየእለቱ አዳዲስና ከፍተኛ የኮቪድ 19 ተጋላጮችን ቁጥር፣ በምታስመዘግብበትና፣ ወደ 113ሺ ሰዎች፣ ሆስቲፓል ተኝተው በሚታከሙበት ጊዜ ነው፡፡
የበሽታ ቁጥጥርና መከላከያው ማዕከል እንደሚለው፣ የፋይዘርን ክትባት ከወሰዱት ሰዎች መካከል፣ 6 የሚሆኑ ሰዎች፣ ከፍተኛ የሆነ የአለርጂ ምልክት የታየባቸው ከመሆኑ በቀር፣ ክትባቱ ዝግጁ በሆነበት ጊዜ፣ ሁሉም ሰው መከተብ እንዳለበት፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ይናገራሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት ብዙ የሚያሰጋ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ ሁኔታውን በቅርብ መከታተላልችንን እንቀጥላለን፡፡ የምናደርገውም ይህንኑ ነው፡፡በብሪታኒያ፣ በአዲስ መልክ እየተስፋፋ ያለው ቫይረስ፣ የበለጠ ተላላፊ ሆኖ የመገኘቱ ዜና፣ የአገሪቱ መሪዎች ሁኔታዎችን እንደገና ወደ መገደብና፣ ወደ መዘጋጋት እንዲመለሱ ያስገደዳቸው መሆኑ፣ እየተነገረ ነው፡፡ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ እና የአውሮፓ አገሮችም፣ ከእንግሊዝ የሚመጡ መንገደኞችን እያገዱ ነው፡፡ የዩናትድ ስቴትስ እና እንግሊዝ መሪዎች ግን፣ አዳዲሶቹ ክትባቶች ወረርሽኙን ሊከላከሉ የሚችሉ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ብዙ ስጋት ሊኖር እንደማይችል ይናገራሉ፡፤ አድሚራል ብሬት ስለዚሁ ሲናገሩ፣ እንዲህ ብለዋል 
ከፊሉ የዩናይትድ ስቴት፣ በተለይም እንደ መካከለኛ ምዕራብና ሰሜን አካባቢ የሚገኙት፣ ወረርሽኙን በተወሰነ ደረጃ መቀነስ ችለዋል፡፡ ያ መሻሻል፣ ችግሩ በከፍተኛ ደረጃ በበረታባቸው፣ በታችኛው የደቡብ አካባቢና በምስራቃዊ ካሊፎርኒያ አካባቢ፣ አልታየም፡፡ የገናን በዓል ለማክበር፣ ጥቂት ቀናት በቀሩበት በዚህ ጊዜ አንኳ፣ አፕል በካሊፎርኒያ የሚገኙ በርካታ መደብሮቹን፣ ለጊዜው ለመዝጋት ወስኗል፡፡
ምን መደረግ እንዳለበት እናውቃለን፡፤ አሜሪካውያን ይህንን ነገር ቢያደርጉ የወርርሽኙን መጠን መቀነስ እንችላለን፡፡ ክትባቱ ከመውጣቱ በፊት እንኳ በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ማዳን እንችላለን፡፤
በመጨረሻም፣ አድሚራሉ እንዲህ አሉ፣ “ወረርሽኙ ለዘለዐለም የሚቆይ ነገር አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎች፣ ይህን አስከፊ የክረምት ጊዜ፣ በአንድነት ተባብረው መሻገር ይኖርባቸዋል፡፡”
(ዘገባው የሚሼል ኩዊን ነው​)
የባይደን እጩ ተሿሚዋ ሊንዳ ቶመስ ስለ አፍሪካ ምርጫ ተናገሩ
            <description>ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጥቁር አሜሪካዊቷን ሊንዳ ቶመስ ግሪንፊልድን በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሰደር አድርገው ማጨታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከኖቬምበር 3ቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፊት፣ የቪኦኤ ዘጋቢ ሻካ ስሳሊ ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ስለምትከለው ፖሊሲ አነጋግራቸው ዘገባ አጠናቅራለች፡፡
ሊንዳ ቶመስ ግሪን ፊልድ፣ በዲፕሎማሲው፣ የ35 ዓመታት ልምድ አላቸው፡፡ በሲዊዘርላንድ፣ ፓኪስታን፣ ኬንያ፣ ጋምብያ፣ በናይጄሪያና ጃማያካ ተዘዋውረው ሰርተዋል፡፡ በላይቤሪያ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሰደር የነበሩ ሲሆን፣ በዩናይትድ ስቴት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ጸሀፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ በአፍሪካ ጉዳይ ከሚያስደንቃቸው መካከል፣ የአፍሪካው መሪዎች፣ ሥልጣን ላይ መቆየት የሚፈልጉበት የጊዜ ገደብ መሆኑን፣ እንዲህ በማለት አበክረው ይናገራሉ፡፡
“በአንዳንድ አገሮች በህገመንግስታቸው የሥልጣን ጊዜ ገደብ አልተቀመጠም፡፡ ስለዚህ ዝምብሎ ከዓመት ወደ ዓመት፣ ለዓመታት ሥልጣን ላይ የሚቆይ ፕሬዚዳንት ይኖርሃል፡፡ እኔ ግን የምለው፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም በአፍሪካ፣ ስኬታማ ሆነናል የምለው፣ የሚካሄዱ ምርጫዎች በሙሉ፣ የጊዜ ገደብን እንደ አንድ መስፈርት አድርገው ሲያስቀምጡ ነው፡፡ ከዚያ ቀጥሎ ሊመጣ የሚገባው ነገር፣ ምርጫዎቹ ፍትሃዊና ግልጽ መሆናቸውን ማረጋገጥና በስልጣን ላይ ያሉት፣ ምርጫውን ላልተወሰነ ጊዜ ሥልጣን ለመቆየት የሚጠቀሙበት መሳሪያ እንዳይሆን ማድረጉ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር በተለይ የሥልጣን ጊዜ ገደብ በሌላቸው አገራት የሚታይ ይመስለኛል፡፡”
ሊንዳ ቶመስ ፣ አፍሪካ ወደ ዘላቂ ልማት እየተሸጋገረች በመምጣቷ፣ በርካታ የዓለም ኃያላን አገራት፣ በአፍሪካ ያላቸው ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱን ሲያስረዱ የሚከተለውን ብለዋል
“ሁላችንም ያ ለውጥ ቀስ በቀስ እየተከስተ መሆኑን እያየን ነው፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ በአህጉሪቱ እንዳለ በግልጽ ከሚታየው ሀብት ጋር የሰው ኃይልም ሀብት ያለ ይመስለኛል፡፡ አፍሪካ ባላት የህዝብ ብዛትም ሆነ ወጣት ታዳጊ አህጉር ናት፡፡ እነዚያ ወጣቶች በአህጉሪቱ ምን መካሄድና አፍሪካ ምን መሆን እንዳለባት ትርክቱን ሲቆጣጠሩትና ሲመሩት እያየን ነው፡፡ በርግጥ የዚያን የለውጥ ፍሬዎች ውጤት ገና አላየንም፡፡ ያን ለውጥ ማየት በምንጀምርበት ወቅት ግን አስደናቂ ነገር የምናይ ይመስለኛል፡፡ በአፍሪካ ትልቅ ተጽእኖ ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ አፍሪካ የመጨረሻው መዳረሻ ምዕራፍ ናት፡፡ ይህን ሁል ጊዜ ነው የምናገረው፡፡ በአፍሪካ አህጉር ያለው እድል በየትኛም የዓለም ክፍል የለም፡፡ ያንን በዓለም ዙሪያ እያየነው ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ አፍሪካውያንም ራሳቸው ከዚያ የመጨረሻው ምዕራፍ ተጠቃሚ የሚሆኑ ይመለኛል፡፡”
ቶመስ ግሪን ፊልድ፣ ለሪፐብሊካን እና ለዴሞክራት ፕሬዚዳንቶች የሠሩ ሲሆን፣ ሁለቱም አስተዳደሮች ለአፍሪካ በሚያደርጉት ትኩረት፣ የጋራ አድናቆት እንዳላቸው ይገልጻሉ፡፡
“እኔ ባለሙያ አገልጋይ ነኝ፡፡ በሁሉም የአስተዳደር ዓይነት ሠርቻለሁ፡፡ በሁለቱም አስተዳደሮች ፖሊሲዎች በሚወጡበት ጊዜ ሁለቱም ፖሊሲዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ በታማኝ የቢሮክራሲው ሙያተኝነቴ አከናውኛቸዋለሁ፡፡ እኔ እንደማስበው እያንዳንዱ አስተዳደር ስትራቴጂያዊ ይሁን ወይም የሞግዚትነት፣ አፍሪካን በሚመለከት ሁለቱም አስተዳደሮች አፍሪካን እንደ አጋርነት የተመለከቱ ሲሆን አፍሪካ ውስጥ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የሞከሩትም በዚያው መንገድ ይመስለኛል፡፡”
ለ35 ዓመታት ያገለገሉት ነበሯ ዲፕሎማት፣ ሊንዳ ቶማስ ግሪን ፊልድ፣ በተባበሩት መንግሥታት፣ የዩናይትድ ስቴትት አምባሳደር ሆነው እንዲሰሩ፣ በባይደን እንደ ተመረጡ፣ በቲውተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ “እናቴ ዓለምን የተሻለች ለማድረግ፣ በደግነት እና በርህራሄ መምራት እንደሚገባ አስተምራኛለች፡፡ በውጭ አገር የአገልግሎት ዘመኔም ያንን ትምርህት ተግባራዊ ሳደርግ ኖሪያለሁ፡፡ አሁንም ሹመቴ ከጸደቀልኝ፣ በተባበሩት መንግሥታት አምባሰደርነቴ፣ ተመሳሳዩን አደጋለሁ” ብለዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
የትራምፕና ባይደን ርክክብ ሲጠበቅ ወረርሽኙ እየከፋ ነው
            <description>በዩናይትድ ስቴትስ የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የ2020 ምርጫ አሸናፊ እንደሆኑ የተነገረላቸው የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ አገሪቱን ፈጥኖ ለመርዳት እንዲችሉ፣ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የርክክቡን ሂደት በዚህ ሳምንት እንዲጀምሩ እየጠየቁ መሆናቸውን የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሼል ኩዪን ዘግባለች፡፡</description>
የባይደን የድል ንግግር፤ ስለምርጫው ውጤት የዓለም ምላሽ
            <description>የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለአንድነትና ተከፋፍሎ የተራራቀውን የፖለቲካ አካሄድ ለማቀራረብ የሚጣራ ንግግር አድርገዋል።</description>
የዩናይትድ ስቴትስ የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ ሹመት ፀደቀ
            <description>የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛነት ያጯቸውን ዳኛ ኤሚ ኮኒ ባረትን ሹመት ትናንት ሰኞ አጽድቋል።
ሪፖብሊካኗ ሴኔተር ሱዛን ኮሊንስ ከመላው የመወሰኛው ዲሞክራት አባላት ጋር ሆነው የዳኛይቱን ሹመት ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል።
 የዳኛ ባረትን ሹመት መፅደቅ የተቃወሙት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው እጅግ በተቃረበበት ጊዜ የመጣ በመሆኑ እንደሆነ ሴነተር ኮሊንስ ገልጸዋል።
 በአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ መሰረት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባልፉት ቢያንስ አንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት ውስጥ በመወሰኛ ምክር ቤቱ አናሳ መቀመጫ ካለው ፓርቲ አንዳችም የድጋፍ ድምፅ ሳይሰጠው ሹመቱ የጸደቀለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ኖሮ አያውቅም።
ዳኛ ባረት ሹመታቸው በመወሰኛ ምክር ቤቱ ከፀደቀ በኋላ በዋይት ሃውስ በተካሄደ ሥነ ስርዓት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ክላረንስ ቶማስ ቃለ መሃላ አስፈጽመዋቸዋል።
በኅዳሴ ጉዳይ የትረምፕ ንግግርና ምላሾች
            <description>ግብፅ ታላቁ ኅዳሴ ግድብን እንድታፈርስ መምከራቸውንና እርምጃውን እንደሚያበረታቱም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ መናገራቸውን ተከትሎ ከተለያዩ አካባቢዎች የተቃውሞ ድምፆች እየተሰሙ ነው።</description>
ፕሬዚደንት ትረምፕ  ነገ ከሆስፒታል ሊወጡ ይችላሉ ተብሏል
            <description>በኮቪድ - 19 ምክንያት ሆስፒታል የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ትረምፕ የደማቸው የኦክሲጂን መጠን ሁለቴ ለአጭር ጊዜ ወርዶ እንደነበረ ፕሬዚደንቱን እያከሙ ያሉት ዶክተሮች ዛሬ ተናገሩ። 
የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ፦ ያለፉ ጉባዔዎች ግምገማ
            <description>የዩናይትድ ስቴትስ አጠቃላይ ምርጫ ሂደት በይፋ ተጀምሯል። የቅድሚያ ድምፅ አሰጣጥ እየተካሄደ ነው። ለዋናው የምርጫ ዕለት የቀሩት ሰላሣ አራት ቀናት ብቻ ናቸው። ባለፈው ወር መጨረሻ የተካሄዱት የሁለቱ አውራ ፓርቲዎች /የሪፐብሊካኑና የዴሞክራቲክ/ ጉባዔዎች ዕጩዎቻቸውን አሳውቀው ሁለቱ ተገዳዳሪዎች፤ ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ዶናል ትረምፕ እና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዚህ ምሽት የመጀመሪያ የግንባር ክርክራቸውን ይገጥማሉ።</description>
የመጀመሪያው የምርጫ ክርክር ኦሃዮ በምትገኘው ክሊቭላንድ ከተማ ይካሄዳል
            <description>ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕንና ዲሞክራቱን የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን ፊት ለፊት የሚያጋጥመው የመጀመሪያው የምርጫ ክርክር ማክሰኞ ኦሃዮ በምትገኘው ክሊቭላንድ ከተማ ይካሄዳል። ክርክሩ ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ፊት ለፊት ቀርበው እንዲያካሂዱ ከታቀደው ሦስት የክርክር መድረኮች የመጀመሪያው ነው።
የዲሞክራትና ሪፖብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች በተቀራራቢ ቁጥር በሚገኙበትና፣ መራጮች ለተፎካካሪዎቹ ያላቸው አመለካከት ከፍተኛ ልዩነት ባሳየበት ኦሃዮ ጨምሮ በጠቅላላ አገሪቱ የሚካሄደው የዘንድሮ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ ዘመቻ ማጠቃለያው እየተቃረበ ነው። የክርክሩን ሂደት ለመከታተል ክሊቭላንድ የምትገኘው ዘጋቢያችን ካሮሊን ፕሬሱቲ የላከችውን ዘገባ ይዘናል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
ኮቪድ19 - ክትባት ለወራት ላይደርስ ይችላል
            <description>ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረ ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ዘጠኝ መቶ ሃምሣ ሰው ለኮሮናቫይረስ መጋለጡ መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር ባወጣው የክትትል ሪፖርት አስታውቋል።</description>
የብላክ ፓንተር ተዋናይ ቻድዊክ ቦዝማን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝና ባተረፈው በብላክ ፓንተር ፊልም የአፍሪካዋ ልብ ወለድ ንጉሣዊ ግዛት  የዋካንዳ ንጉሥ ቲ ቻላን ሆኖ ባሳየው የላቀ የተዋናይነት ጥበብ ዕውቅና ያገኘው ቻድዊክ ቦዝማን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ቻድዊክ በአርባ ሶስት ዓመቱ በአንጀት ካንሰር ህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ታውቋል
ቻድዊክ ቦዝማን እ አ አ ከ2016 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ስለህመሙ ይዞታ ያወቀ ቢሆንም መታመሙን በይፋ ሳይናገር በታላላቅ የሆሊዉድ ፊልሞች ስራውን ያለማቋረጥ መቀጠሉ ተገልጿል
በማህበራዊ መገናኛ ገጹ ላይ የወጣው መግለጫ ታሞም "ለሙያው በነበረው ክብር በብላክ ፓንተር ፊልም ለንጉሥ ቲቻላን ዕውን ማድረግ ነበረበት" ሲል አስቀምጦታል
 ቻድዊክ ቀደም ብሎም ስመ ጥር ጥቁር አሜሪካውያን ፈርጦችን ተመስሎ በተዋናይነት ተጫውቷል ፥ ጥቁር አሜሪካዊው የቤዝቦል ተጫዋች ጃኪ ሮቢንሰንን 42 በተሰኘው ፊልም  ዕውቁን ድምጻዊ ጄምስ ብራውንን ጌት ኦን አፕ በተባለው ፊልም ተጫውቶ አድናቆት አትርፏል
በቅርቡም በስፓይክ ሊ  በተዘጋጀው ዳ ፋይቭ ብለድስ በተባለው ፊልም ተዋናይ ነበር 
የካሊፎርኒያው  ሰደድ እሳት ዛሬም ቀጥሏል
            <description>የምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስዋ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የተዛመተው የደን ሰደድ እሳት ዛሬም ቀጥሏል
አገረ ገዥው ጋቪን ኒውሰም ቃጠሎውን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ እገዛ ተማጽነዋል
ወደ አምስት መቶ ስድሳ በሚጠጉ ስፍራዎች በክፍለ ግዛቱዋ ዙሪያ የተቀሰቀሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት አስራ ሁለት  ሺህ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እይተረባረቡ ናቸው
በሰደድ እሳቱ እስካሁን ቢያንስ አምስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ጨምሮ አርባ ሶስት ሰዎች ተጎድተዋል፥ ያሁኑ የአየር ሁኒታ ቃጠሎውን ያባብሰዋል የሚል ስጋት አለ
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ  አድርጉ ያልኩዋቸውን ስላልሰሙ ነው ብለው ለቃጠሎው የክፍለ ግዛትዋ አስተዳዳሪዎች ወቅሰዋል
 ጫካው ውስጥ ለዓመታት የተከመረውን ቅጠሉን እና የወደቀ ዛፍ ጥረጉ ብያቸው ነበር ብለዋል
የዩናይትድ ስቴትስ ቆጠራና ኢትዮጵያውያን
            <description>በዩናትድ ስቴትስ በየአስር ዓመቱ አንዴ የሚደረገው የህዝብ ቆጠራ ዘንድሮም ይካሄዳል፡፡ የቆጠራው መጠናቀቂያ ጊዜ ከህዳር ወደ መስከረም እንዲያጥር በመደረጉ ሊጠናቀቅ የቀሩት ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ምን ይመስላል?</description>
ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችዋን ከጀርመን እያወጣች ነው
            <description>ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ በመላው ዓለም ያላትን የሠራዊት ቁጥር ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ 12ሺ የሚጠጉ ወታደሮቿን ከጀመርን እያወጣች ነው፡፡ ከዋሽንግተን የቪኦኤ ዘጋቢ ሲንዲ ሴን ያጠናቀረቸው ዘገባ እነሆ፡፡
ሴንት ፖል - ሚኔሶታ፤ የኢትዮጵያዊያን ሠልፍና ሻማ
            <description>ሚኔሶታ ዋና ከተማ ሴንት ፖል ውስጥ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ትናንት ምሽት ላይ ሻማ የማብራት ሥነ ሥርዓት አድርገዋል።</description>
የዩናይትድ ስቴትስ ጠ/ፍ/ቤት ስለጥገኝነት ይግባኝ
            <description>የዩናይትድ ስቴት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአሜሪካ የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ማመልክቻቸው በኢምግሬሽን ባለሥልጣናት ውድቅ የተደረገባቸው "ይግባኝ የማለት ሕገመንግሥታዊ መብት የላቸውም" ሲል ወስኗል፡፡
ሰኔ 18/2012 ዓ.ም. የተላለፈው ይህ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ብዙዎቹን ጥገኝነት ጠያቂዎች ከሃገር ማባረር ለሚፈልገው የአሁኑ አስተዳደር ድርጊቱን እንዲገፋበት የሚያበረታታው መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የትናንቱ ዕለታዊ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ቁጥር ከፍተኛው ነው
            <description>በዓለም ዙሪያ  ትናንት ቅዳሜ ብቻ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተመዘገበው ሰዎች ቁጥር እስከዛሬ በሃያ ሰዓት ውስጥ ከተገኙት ሁሉ ከፍተኛው መሆኑ ተገለጸ
ሁለት  መቶ አስራ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስድስት አዲስ የቫይረስ  መመዝገቡን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል
ካሁን ቀደም የታየው ከፍተኛ ዕለታዊ የአዲስ ተጋላጮች አሃዝ ባለፈው ሳምንት ዕሁድ አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሰባ ሰባት እንደነበር ይታወሳል
በበሽታው ምክንያት አሁንም በቀን ቁጥሩ አምስት ሺህ ለህልፈት እየተዳረገ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትናንትና ብቻ ሃምሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሁለት የቫይረሱ ተጋላጮች የተመዘገቡ ሲሆን አጠቃላዩ ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ ሺህ አልፏል
 ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንትየነጻነት ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ በዋይት ሐውስ ባስተናገዱት ዝግጅት ባሰሙት ንግግር በሀገሪቱ በኮቪድ አስራ ዘጠኝ ምክንያት አንድ መቶ ሰላሳ  ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን አላነሱም፤ ሃገሪቱ ቫይረሱን መዛመት ለመግታት እየታተረች ቢሆንም ፕሬዚደንቱ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ  ስትራተጂያችን በጥሩ ሁኔታ እየተራመደ ነው ብለዋል
እስከዓመቱ መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ ክትባቱን ወይም መድሃኒቱን ማግኘታችን አይቀርም ሲሉም ተናግረዋል
በሳይንቲስቶች ዕምነት ግን በዚሁ ዓመት ውስጥ ከተገኘ በሚያስገርም ሁኒታ ከተፋጠነ ብቻ ነው ባዮች ናቸው
የረዥም ዘመን የማሕበረሰብ ግልጋሎት ሲከበር
            <description>ኮቪድ 19 ባመጣው ለውጥ ሳቢያ በጊዜው መቅረብ ሳይችል የቀረ ቀደም ሲል የተካሄደ ቃለ ምልልስ ነው።</description>
“ኦባማኬር” እንዲሠረዝ ዋይት ሃውስ ‘አቤት’ አለ
            <description>በምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረኃይል በሁለት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል።</description>
ከሰሃራ በረሃ የተነሳ አቧራ ሚክሲኮ ደረሰ
            <description>አትላንቲክ ውቅያኖስን ያቋረጠ ግዙፍ የሰሃራ የአቧራ ማዕበል ሜክሲኮ ጠረፍ ላይ ያሉ ከተሞችንና ዩካታን ባህረሰላጤ ላይ የሚገኙ የመዝናኛ አካባቢዎችን አልብሷል።</description>