ዋሽንግተን በዚህ ሳምንት

Your browser doesn’t support HTML5

ሩሲያ ያለምንም በቂ ምክንያት በአጎራባቿ ዩክሬን ላይ የከፈተቸው ጦርነት አምስት ሳምንት ሞላው፡፡ ዛሬ ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ተፈናቅለዋል፡፡ ምንም እንኳ ክሬምሊን ውጊያው በምስራቃዊ የሃገሪቱ ክፍል ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን ቢገልጽም፣ ሩሲያ መላውን ዩክሬን መደብደቧን ቀጥላለች፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን በአውሮፓው ጉዟቸው የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን “ሥልጣን ላይ መቆየት አይችሉም” ብለው ተናገረዋል፡፡ ይሁን እንጂ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ወደ ኋላው ላይ በሰጡት ማብራሪያ ዋሽንግተን የአገዛዝ ለውጥ እየፈለገች አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡