የፊልሙ ጸሓፊ እና አዘጋጅ ሰማኝጌታ አይችሉህም፣ "እኔ መምከር በምችልበት ዕድሜ ላይ ባለመኾኔ፣ ድራማው ከማስተማር ይልቅ ጠያቂ እና ደንበር ተሻጋሪ የኾነ ሐሳብ እንዲኖረው ማድረግ ላይ አተኩሪያለኹ፤" ብሏል፡፡
በ"ጉዞ ፊልሞች" የተዘጋጀው ይኸው ተከታታይ ድራማ፣ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በቃና ቴሌቭዥን በኩል ለእይታ እንደሚበቃ፣ የፊልሙ ዲሬክተር፣ ጸሓፊ እና አዘጋጅ ሰማኝጌታ አይችሉህም ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል።
ወጣት የፊልም ባለሞያዎቹን ሰማኝጌታን አይችሉህም እና ሲኒማቶግራፈር ጋድ ክፍሎም ጋራ ቆይታ አድርገናል። ከተያያዘው ፋይል ሙሉውን ይከታተሉ።