በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሆንግ ኮንግ ምርጫና የዩናይትድ ስቴትስ እርምጃ እያነጋገረ ነው


የአዲሱ ህዝባዊ ፓርቲ አባላት የሆንግ ኮንግ የምክር ቤት ህግ አውጭዎችን ምርጫ በአሸነፉበት ወቅት እአአ ታኅሳስ 20/2021
የአዲሱ ህዝባዊ ፓርቲ አባላት የሆንግ ኮንግ የምክር ቤት ህግ አውጭዎችን ምርጫ በአሸነፉበት ወቅት እአአ ታኅሳስ 20/2021

በቻይና ተጽዕኖ ሥር ሆኖ ተካሂዷል በተባለው የሆንግ ኮንግ የመጀመሪያው የህግ አውጭ የምክር ቤት አባላት ምርጫ፣ የባይደን አስተዳደር ቻይናን ሊቀጣ ይገባል ወይስ አይገባም በሚለው፣ የዩናትድ ስቴትስ ታዛቢዎች የተለያየ አቋም መያዛቸው ተገለጸ፡፡

ባላፈው እሁድ በተካሄደው ምርጫ የቻይና ደጋፊ የሆኑትና ነባሮቹ እጩዎች 90 ከሚሆነው የምክር ቤቱ መቀጫ 89ኙን አሸንፈዋል፡፡

በባለሙያዎቹ ዘንድ ይህ በእንግሊዝ ቅኝ ስር በነበረችውን ሆንግ ኮንግ የነበሩትን የዴሞክራሲ ኃይሎች ድምጽ ጠራርጎ ያጠፋል የሚል ስጋት ማሳደሩ ተመልክቷል፡፡

ቤጂንግ የምርጫውን ህግ ባለፈው መጋቢት ከቀየረች በኋላ ብዙዎቹ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ላለመሳተፍ ወስነዋል፡፡

“ዲሞክራሲያዊ አይደለም” በሚል ከተቃወሙት አንዳንዶቹ ሲታሰሩ ሌሎች አገር ትተው መሰደዳቸው ተዘግቧል፡፡

በዚህ ምርጫ የነበረው የመራጭ ተሳትፎም 30 ከመቶ መሆኑ ተነገሯል፡፡

የባይደን አስተዳደር ባለፈው ሰኞ እንደ ሰባቱ የኢንደስትሪ አባል አገሮች ጋር በመሆን ካሰማው የጋራ ተቃውሞ ሌላ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ከሆኑ አምስት ዋነኞቹ አገሮችም ጋር በመሆን

በሆንግ ኮንጎ እየተሸረሸረ ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓትና መሰረቶች አሳሳቢ መሆናቸውን የሚያመልክቱ መግለጫዎችን ማውጣቱ ተነግሯል፡፡

መግለጫዎቹ ቻይና እንደ እኤአ በ1997 ሆንግ ኮንግን ከእንግሊዝ መልሳ ከመረከቧ በፊት እኤአ በ1984 የገባችውን ዓለም አቀፍ ግዴታና ስምምነት እንድታከብር ይጠይቃሉ፡፡

በስምምነቱ መሰረት፣ ቤጂኒግ ለሆንግ ኮንግ ከፍተኛ የሆነ የራስ ገዝ ነጻነት እንድትሰጥና ፣ በቻይናም ስር ብትሆን፣ ለ50 ዓመታት እንደ ልዩ ግዛት ነጻነትነቷን እንድትጠብቅ ያሳስባሉ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የባይደን አስተዳደር ባላፈው ሰኞ፣ መሠረታቸውን ሆንግ ኮንግ ውስጥ ባደረጉ አምስት የቻይና ቢዝነስ ተቋማት ጋር የሚሰሩ፣ የውጭ ፋይናንስ ተቋማት ላይ ሁለተኛውን ማዕቀብ መጣሉን አስታውቋል፡፡

የመጀመሪያው ማዕቀብ የተጣለው የከተማዪቱን ነጻነት አልጠበቅችሁም በሚል ባለፈው ሀምሌ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አንዳንድ ባለሙያዎች፣ በቻይና የተጣሰውን ስምምነት እንግሊዝ ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በመውሰድ ሆንግ ኮንግን ልትታደጋት ትችላለች የሚል መከራከሪያ ማንሳታቸው ተገልጿል፡፡

ሌሎች ደግም “ቻይናን እጅ መጠምዘዙም ሆነ ግፊት ማድረጉ ያበቃለት ጉዳይ ነው፡፡ ሆንግ ኮንግ የቻይና አካል ሆናለች፡፡ ካርዱ ያለው በቻይና እጅ ነው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG