ስፔይን ማድሪድ በሚገኘው የዩክሬን ኤምባሲ ውስጥ የሚሰራው አንድ ሠራተኛ በከፈተው ደብዳቤ ውስጥ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ መጎዳቱ ከተሰማ በኋላ ዩክሬን በውጭ አገር የሚገኙ ኤምባሲዎችዋን ጥበቃ ማጠናከሯ ተነገረ፡፡
ዛሬ ረቡዕ ቀላል ጉዳት የደረሰበት የኢምባሲው ሰራተኛ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ ተገልጿል፡፡
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ በውጭ የሚገኙ የዩክሬን ኤምባሲዎች በሙሉ በአስቸኳያ ጥበቃቸውን እንዲያጠናክሩ ማዘዛቸውን ከሚኒስቴሩ የወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡
የስፔይኑ አቻቸውም የጥቃቱን መንስኤ እንደሚረመር እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ያሳሰቡ ሲሆን ጥቃቱን ያደረሰው አካል ማንም ቢሆን ዩክሬንን ሊያስፈራራ አይችልም ማለታቸው ተዘግቧል፡፡