በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ፓኪስታን ስለሚገኙ ዜጎቿ ደህንነት የሰጠችውን አስተያየት ፓኪስታን ግራ የሚያጋባ አለችው


የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሙምታዝ ባሎክ
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሙምታዝ ባሎክ

ቤጂንግ በዚያች አገር ያሉ ዜጎቿን ደህንነት አስመልክቶ የሰነዘረችውን ትችት ውድቅ ያደረገችው ፓኪስታን “ግራ የሚያጋባ” እና በጎረቤት ሃገሮች መካከል መሰረት የጣለ ዲፕሎማሲያዊ ሥርአት የሚቃረን ብላዋለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሙምታዝ ባሎክ ኢስላማባድ በተካሄደው ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ሲናገሩ የአገራቸው መንግስት በፓኪስታን ለሚገኙ የቻይና ዜጎች፣ በዚያ ስለሚካሄዱ ፕሮጀክቶች እና ተቋማትን ደህንነት መረጋገጥ ትኩረት ይሰጣል” ብለዋል። ባሎክ ይህን የተናገሩት ፓኪስታን በሃገሯ ለሚገኙ በርካታ ቻይናውያን ሰራተኞች መገደል ምክኒያት ተጠያቂ በሆኑ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰድ አለባት’ ሲሉ በኢዝላማባድ የቻይና አምባሳደር ጂያንግ ዛይዶንግ የሰነዘሩት ያልተለመደ ማሳሰቢያ ተከትሎ ነው።

ጂያንግ ሁከቱን “ተቀባይነት የለሌለው” ሲሉ ‘ቤልት ኤንድ ሮድ’ በተሰኘው የቻይናው የመሰረተ ልማት ግንባታ ይታደናቅፋል ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG