ዋሺንግተን ዲሲ —
የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን ከፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ጋር ለአራት ቀናት ያህል ለመነጋገር ቻይና ገብተዋል።
ኪምና ባለቤታቸውሪ ሶል ጁ ከበርካታ ከፍተኛ ባለሥጣኖች ጋር ሆነው በልዩ ባቡር ዛሬ ቤዢንግ ገብተዋል። የሰሜን ኮርያ የዜና አገልግሎት በዘገበው መሰረት ኪም ቻይና የተጓዙት በፕሬዚዳንት ሺ ግብዣ ነው።
ኪም ካለፈው ዓመት አንስቶ ቻይናን ሲጎበኙ ለአራተኛ ጊዜ ነው። ይህም ኪም ዦንግ ኡንና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶንናልድ ትረምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ስብሳባ ሊያደርጉ ይችላሉ የሚል ጭምጭምታ አስነስቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ