"የመፈንቅለ መንግሥት ሒደት ቅጥያ ነው" - የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሹም
ከህወሓት አመራሮች ውዝግብ ጋራ በተያያዘ ላለፉት መቶ ቀናት በዝግ የቆየው የመቐለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት፣ ዛሬ ኀሙስ፣ በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በሚመራው ቡድን ቁጥጥር ሥር ውሏል።
በጊዜያዊ አስተዳደሩ የከተማዋ ከንቲባ እንዲኾኑ የተሾሙት አቶ ብርሃነ ገብረ ኢየሱስ፣ "ጽንፈኛ" ሲሉ የጠሩት ቡድን በወታደራዊ አመራሮች ድጋፍ ጽሕፈት ቤቱን እንደተቆጣጠረ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፤ "የመፈንቅለ መንግሥት ሒደት ቅጥያ ነው፤" ሲሉም ድርጊቱን ኮንነዋል።
በዶር. ደብረ ጽዮን ሊቀ መንበርነት በሚመራው የህወሓት ቡድን የመቐለ ከተማ ከንቲባ እንዲኾኑ ታጭተው በከተማዋ ምክር ቤት የተሾሙት ዶክተር ረዳኢ በርሀ በበኩላቸው፣ "ወደ ጽሕፈት ቤቱ የገባነው በሰላማዊ መንገድ ነው፤" ሲሉ ተናግረዋል።
ተቀማጭነታቸው በዐዲስ አበባ ከተማ የኾኑ የዩናይትድ ስቴትን ጨምሮ የ25 አገሮች ኤምባሲዎች፣ በሰሜን ኢትዮጵያ እያገረሸ ያለውን ውጥረት በቅርበት እየተከታተሉት እንደሚገኙ ገልጸው፣ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ጠይቀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም