በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪታንያ ፖሊሶች ማንቸስተር ከተማ በደረሰው የሽብርተኛ ጥቃት ተጨማሪ ሰዎችን አስረዋል


የብሪታንያ ፖሊሶች ባለፈው ሣምንት ማንቸስተር ከተማ ውስጥ ከደረሰው የሽብርተኛ ጥቃት በተያያዘ ተጨማሪ ሰዎችን አስረዋል።

የብሪታንያ ፖሊሶች ባለፈው ሣምንት ማንቸስተር ከተማ ውስጥ ከደረሰው የሽብርተኛ ጥቃት በተያያዘ ተጨማሪ ሰዎችን አስረዋል።

እስካሁን የታሠሩት ሰዎች ቁጥር አሥራ አራት ደርሷል።

የፀረ ሽብርተኛ ሕግ የጣሰ ተግባር በመፈፀም ተጠርጥሯል የተባለ አንድ የሃያ ሦስት ዓመት ወጣት ዛሬ ማንቼስተር ውስጥ ተይዟል። ትናንትም እንዲሁ በዚያው ከተማ አንድ የሃያ አምስትና የአሥራ ዘጠኝ ዓመት ወጣቶች በተመሳሳይ ወንጀል ጥርጣሬ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የዛሬ ሳምንት ሰኞ ማንቼስተር አሬና ላይ ከታየው የአሜሪካዊቱ ፖፕ ሙዚቃ ድምፃዊት አሪያና ግራንዴ የሙዚቃ ድግስ በኋላ በደረሰው አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት ሃያ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ከመቶ በላይ ቆስለዋል። ጥቃቱን ያደረሰው ሳልማን አቤዲ የሚባል የሃያ ሁለት ዓመት ወጣት የማንቸስተር ነዋሪ መሆኑን የቢሪታንያ ፖሊስ አስታውቁዋል።

ወንድሙና አባቱ ሊቢያ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ሊቢያ ውስጥ ታስረዋል።

ከጥቃቱ በተያያዘ በጠቅላላው አሥራ ሥድስት ሰዎች የተያዙ ሲሆን ሁለቱ ክስ ተለቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG