በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኩዌት ከአደገኛ ዕጽ ጋራ በተያያዘ የታሰሩ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ጨምሮ አሜሪካዊ እስረኞችን ለቃለች


በአሜሪካዊያን ታጋቾች እና እስረኞች ጉዳይ የሚሰሩት አማካሪው ጆናታን ፍራንክ በኩዌት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ እአአ መጋቢት 12/2025
በአሜሪካዊያን ታጋቾች እና እስረኞች ጉዳይ የሚሰሩት አማካሪው ጆናታን ፍራንክ በኩዌት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ እአአ መጋቢት 12/2025

ኩዌት ከአደገኛ ዕፅ ጋራ በተያያዘ ክስ ተመስርቶባቸው ለዓመታት በእስር ላይ የነበሩ የቀድሞ ሠራዊት አባላትና እና የወታደራዊ ተቋራጭ ሠራተኞችን ጨምሮ አሜሪካውያን እስረኞችን ለቃለች።

የአሜሪካ መንግሥት በውጭ ሀገር የታሰሩ አሜሪካውያንን አስለቅቆ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ባደረገው ጥረት የተፈቱት እስረኞች ወደ ኒውዮርክ ተወስደዋል፡፡

እስረኞቹ የተለቀቁት በቅርቡ ዋናው የትረምፕ አስተዳደር የታጋቾች ጉዳይ መጓዛቸውን ተከትሎ መኾኑም ተመልክቷል፡፡

በአሜሪካዊያን ታጋቾች እና እስረኞች ጉዳይ የሚሰሩት አማካሪው ጆናታን ፍራንክ እስር ላይ ከነበሩ ስድስት እስረኞች ጋራ በመኾን ለኩዌት መንግሥት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን “ደንበኞቼና ቤተሰቦቻቸው የኩዌት መንግሥት ላሳየው ሰብአዊነት ምስጋናቸውን ያቀርባሉ”ሲሉም በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡ ደንበኞቻቸው ጥፋት የሌለባቸው ንጹሐን መኾናቸውንም ፍራንክ አያይዘው ገልጸዋል።

ምንም እንኳን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ሁኔታው ምንም ዐይነት አስተያየት ባይሰጥም፣ ከኩዌት እስር ቤት ተጨማሪ አሜሪካውያን እስረኞች ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በነዳጅ የበለጸገችው እና በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር የሆነችው ኩዌት፣ ጉልህ የሆነ የአሜሪካ ጦር ኅይል የሠፈረባት እና ብዙ የአሜሪካ ሥራ ተቋራጮች የሚገኙባት ሀገር ናት፡፡

ኩዌት በርካቶችን ለእስር የዳረጋቸውን ጠንካራ የአደገኛ እፅ ሕግጋትን የምታስፈጽም ሲሆን እስረኞች ላይ የተለያዩ የሰብአዊ አያያዝ በደሎች እንደሚፈጸሙ ቤተሰቦች ይናገራሉ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኩዌት የአደገኛ እፅ ሕጎች፣ የሞት ቅጣትን ጨምሮ ረጅም እስራት እና ከባድ ቅጣት እንደሚያስከትሉ ያስጠነቅቃል፡፡

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ ሥልጣን ከተመለሱ በኋላ አስተዳደራቸው ከሩሲያዊው ማርክ ፎጌል እና ከቤላሩስ የመጣውን ሌላ አሜሪካዊ ዜጋን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ በርካታ አሜሪካውያን እንዲፈቱ አድርጓል።


🟢 የቪኦኤ ዋትስአፕ ቻናል ይከተሉ

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG