በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሄይቲ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ደረስ


በደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል
በደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል

በሬክተል ስኬል፣ 7.2 ይሆናል በተባለው የመሬት መንቀጥቀጡ አደጋ፣ ከሰዎች ህልፈት በተጨማሪ፣ በርካታ ህንጻዎች የወደሙ ሲሆን፣ ቢያንስ የሁለት ከተሞች የመገናኛ መስመር ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል፡፡

አደጋው የደረሰው የዛሬ 11 ዓመት ተመሳሳይ መጠን ያለው አደጋ ከደረሰባት የሴንት ሉዊስ ደ ሳድ ከተማ 12 ኪሎ ሜትርእንዲሁም ከዋና ከተማ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኝ ፐቲት ትሯደ ኒፕስ በምትባል ስፍራ ነው፡፡

በወቅቱ በደረሰው አደጋ፣ ወደ 220 ሺ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ፣ መጠለያ አልባ የሆኑ አስር ሺዎች ደግሞለአንድ ዓመት በድንኳን እንዲቆዩ ማድረጉም ይታወሳል፡፡

አሁን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋም የመጣው፣በቅርቡ በተገደሉት ፕሬዚዳንት ጃኔል ሞይሴ ምክንያት፣ በፖለቲካ ቀውስ እየታመሰች በምትገኘው ሄይቲ መሆኑን ተነግሯል፡፡

ስለ ሁኔታው ማብራሪያ የተሰጣቸው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን፣ አደጋው የደረሰው ሌላ ፈተና ላይ በሚገኘው የሄይቲ ህዝብ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑም ፕሬዚዳንቱ የዩናይትድ ሴቴትስ የልማትና ተራድኦ ድርጅት አስተዳዳሪ ሰማንታ ፓወር፣ ለአገሪቱ የሚያስፈልገውን አስቸኳይ እርዳታ እንዲያቀናጁ ማዘዛቸውን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG