በዩናይትድ ስቴትስ ልክ የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጥር ኅዳር 5 ቀን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ይካሄዳል፡፡ የመራጭ አስተያየት ግምገማዎች እንደሚያመለክቱት የግሪን ፓርቲ እጩ ተፎካካሪ ጂል ስታይን 1 ከመቶ ገደማ የሚሆነውን ድምጽ ያገኛሉ፡፡
ይሁን እንጂ የእርሳቸው መወዳደር በምርጫው ውጤት ላይ ትልቅ አንድምታ ሊኖረው ይችላል፡፡አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ከወዲሁ እንደሚተነብዩት እጅግ ተቀራራቢ በሆነ የመራጭ ድጋፍ ብርቱ ፉክክር በሚካሄድባቸው ግዛቶች ጂል ስታይን የሚወስዱት ድምጽ እጅግ ጥቂት ቢሆን እንኳን ማን እንደሚያሸንፍ ወሳኝ ሊሆን ይችላል፡፡
ማክሲም አዳምስ ከዋሽንግተን ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይይ ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም