የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው በሱሰ ውስጥ ያለፉ ወጣቶች፥ የአልኮል መጠጥን፣ ሲጋራንና ጫትን ጨምሮ እንደ ቀልድ የጀመሯቸው ሱስ አማጭ ልምምዶች፣ እያደር ሕይወታቸውን እንዳመስቃቀሉባቸውና የጤና እክልም እንዳመጡባቸው ነግረውናል፡፡
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የሥነ ልቡና ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ የወጣቶች የሱስ ተጋላጭነት እያስከተለባቸው ካለው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ባለፈ፣ ለአእምሮ ጤና ሕመምም ምክንያት እየኾነ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡
አስማማው አየነው በዚኽ ጉዳይ ላይ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል።