ርቲስት አንዱዓለም ጎሣ ተጨማሪ 13 ቀናትን በእስር እንዲቆይ ፍርድ ቤት ፈቀደ
ባለፈው ሰኞ ሌሊት፣ ከምትኖርበት ሕንፃ አምስተኛ ፎቅ ላይ ቁልቁል ወድቃ ሕይወቷ ካለፈው፣ ሞዴል እና የማስታወቂያ ባለሞያ ቀነኒ አዱኛ ሞት ጋራ በተያያዘ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የሚገኘው እጮኛዋ አርቲስት አንዱዓለም ጎሣ፣ ተጨማሪ 13 ቀናትን በእስር ቆይቶ ምርመራ እንዲቀጥል ፍርድ ቤት አዘዘ።
የዐዲስ አበባ ፖሊስ፣ ከቀነኒ ሞት ጋራ በዋና ወንጀል አድራጊነት የጠረጠረው አንዱዓለምን እንደኾነ በመግለጽ፣ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ የነበረ ሲኾን፣ ከጠበቃው ጋራ ፍርድ ቤት የቀረበው አንዱዓለም ደግሞ፣ የቀነኒ ሕይወት ያለፈው በአደጋ እንደኾነ በመግለጽ ከእስር እንዲፈታ አመልክቶ ነበር።