በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ:- የሰላም መንገዶች - ልዩ የቴሌቪዥን ውይይት


ኢትዮጵያ:- የሰላም መንገዶች - ልዩ የቴሌቪዥን ውይይት
please wait

No media source currently available

0:00 0:57:50 0:00

ኢትዮጵያ:- የሰላም መንገዶች - ልዩ የቴሌቪዥን ውይይት

“ኢትዮጵያ፤ የሰላም መንገዶች” በሚል ርዕስ የተሰናዳ የአንድ ሰዓት ተኩል ውይይት በአሜሪካ ድምፅ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት ተዘጋጅቷል። የተለያዩ ሐሳቦች ያሏቸው ትውልደ ኢትዮጵያ በአንድ ስቱዲዮ ውስጥ ተቀምጠው በአንድ መድረክ ላይ ሐሳባቸውን አንሸራሽረዋል።

ውይይቱ ሚሊዮኖችን ለህልፈት፣ ለመፈናቀል፣ ለስደትና ለእንግልት የዳረገውን ቀውስና ዛሬ ፈትሿል። የሰላም መንገዶች ምንድናቸው? እንቅፋቶች ይኖሩ ይሆን? በተወያዮቹ የተዳሰሱ ሐሳቦች ናቸው። ኢትዮጵያ የሰላም መንገዶች በዚህ ጥያቄ ላይ ተንተርሶ የተሰናዳ ዝግጅት ነው፡፡ በተለይ በውጭ ሀገር የሚኖረው ትውልደ ኢትዮጵያ በትውልድ ሀገሩ ላይ ሰላም እንዲሰፍን አንድነቷና ሉዓላዊነቷ እንዲጠበቅ ወደ ልማትና እድገት እንዲዘልቅ ሊያግዝ የሚችል ገንቢ ሚና ሊጫወት ይችል ይሆን የሚለው በሰፊው ተሰራጭቷል፡፡

የመድረክ ተወያይ እንግዶች የነበሩት አቶ ሄኖክ አበበ የሕግ ትምህርት አጥንተዋል፡፡ አቶ ሄኖክ በኢትዮጵያ ጉዳዮችም በጥናት ላይ ቆይተዋል አሁን የሚኖሩትና የሚሠሩት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ነው፡፡

ወ/ት መዓዛ ግደይ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያና ኦምና ትግራይ በተባለ የትግራይ ተወላጆች መብት ተሟጋች ዓለም አቀፍ ድርጅት ማኅበረሰብ አደራጅ ናቸው፡፡ በትግራይ የመጀመሪያው የነጻ ሴቶች መብት ንቅናቄ ተብባሪ መስራችም ናቸው፡፡

ረዳት ፕሮፌሰር ኢታና ሀብቴ በተፈጥሮ አካባቢ ታሪክ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ታሪክ እንዲሁም በኦሮሞ የኢትዮጵያ ታሪክ ጽሁፎች ምርምሮችን ያካሂዳሉ፡፡ በጀምስ ማዲስን ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፈሰር የሆኑት ዶ/ር ኢታና የአፍሪካ ታሪክና የዓለም ታሪክ መምህርም ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ የሰላም መንገዶች የስቱዲዮ ተወያዮች
ኢትዮጵያ የሰላም መንገዶች የስቱዲዮ ተወያዮች

በስካይፕ መስመር ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው በኒዮርኩ የኢዮና ኮሌጅ የኅብረተሰብ ጥናት እንዲሁም እድገትና ጥናት ትምህርት ክፍል መምሕር ናቸው፡፡ የማኅበረሰብ የሰው ዘር የብሄረሰቦች ግንኙነት ቤተሰብና ማኅበረሰብ እንዲሁም ማኅበራዊ ችግሮች ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን ያስተምራሉ፡፡

አቶ ዓለማየሁ ፈንታሁ የሕግ ባለሙያና ተንታኝ ናቸው፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ህገ መንግስታዊ ህግ ፌደራሊዝምና የሰብዓዊ መብቶችን አስተምረዋል፡፡ የግጭት ትንታኔና አፈታት ጥናት አዋቂም ናቸው፡፡

ዶ/ር ዓለማየሁ ብሩ የፖለቲካ ፍልስፍና አዋቂ ናቸው፡፡ በቨርጂኒያ ግሎባል ዩኒቨርስቲና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፍልስፍና አስተምረዋል፡፡

ሦስት የስካይ ተጋባዥ ተወያዮች
ሦስት የስካይ ተጋባዥ ተወያዮች

ለተናጋሪዎች ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል የፕሪቶሪያውንና የናይሮቢውን የአፈጻጸም ስምምነት ተክትሎ መንገድ ተከፍቶ እርዳታ ወደ ክልሉ እየገባ መሆኑን ዓለም አቀፍ የረድኤት ተቋማት የኢትዮጵያ መንግሥትና የክልሉ አስተዳደር በተመሳሳይ ይፋ አድርገዋል፡፡

ሌሎችም የስምምነቱ ሂደቶች እየተካሄዱ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡ በስምምነቱ መሰረት አገሪቱ ወደ ሰላም ጎዳና እንድትመጣ የተያዘው ጥረት እንዴት ይገመገም ይሆን? የሚለው እንዲሁም "በተለይ ደም መፋሰሱን ተከትሎ ስለተባባሰው የጥላቻ ስሜት እና ስለድቀነው ፈተና ምን ይላሉ ህዝቦችን አብሮ የሚያኗኑርስ ጤናማ ሁኔታስ እንዴት ይፈጠራል?" የሚሉት ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

እጅግ የከፋ እልቂት ያስከተለውን ጦርነትና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚፈጸሙ ግድያዎችን ተከትሎ በሁሉም ወገን እጅግ የተካረሩ ሁኔታዎችን ተመልክተናል እንዳለመታደል ሆኖ የተፈጠረው መቃቃርና በጸብ መታየቱ እንግልት በበዛበት ህዝብ ዘላቂ ሰላም ላይም ማጥላቱ አልቀረም ግለሰቦች ይልቁንም ልሂቃኑ የሚያራምዱት የጥላቻ ስሜት እንደተባለው የማህበረሰቦችን አብሮ መኖር አደጋ ላይ የጣለው ከሆነ አንድ አገር አንድ ምድር ላይ መሆኖራቸው ላይቀር ወይንም አንዱ አንዱን አጥፍቶ ላይጨርስ ከዚሁ ጥላቻ ትርፉ መጨረሻው ግቡ ምንድነው ጥያቄዎችም በውይይቱ የቀረቡ ነበሩ፡፡

ተናጋሪዎቹ በፕሪቶሪያና ናይሮቢ ላይ ትልቅ እመርታ ነው ማለት እንችላለን ሲካሄድ የነበረውን ደም አፋሳሽ ውጊያ ማስቆም መቻሉ ትልቅ ነገር መሆኑን ገልጸው ለዘለቂነቱ መመለስ የሚኖርባቸው ጥያቄዎችና የግጭት መንስኤ የሆኑ መሰረታዊ ምክንያቶች መታየት አለባቸው ብለዋል፡ ሰሜን ኢትዮጵያ ወይም ትግራይ ላይ የተፈጸመው ጦርነትና አሁን ደግሞ ስምምነት መኖሩ ለኢትዮጵያ ሰላም የሚሰጥ ብቸኛ ስምምነት አለመሆኑን ተናጋሪዎች አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የህዝብ ጥያቄ መሰረት ያላደረገ በመሪዎች ብቻ የሚደረግ ስምምነት ግቡን ይመታል ወይ የሚልን ከራሳችሁ ማህበረሰብ አልፋችሁ ለሌሎች ማህበረሰቦች ሞትና በደል መቆርቆረ የምትጀምሩት መቼ ነው በሚል ከድማጮች ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ተስጥቷል፡፡

/ሙሉ ውይይቱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG