በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለአሜሪካ የቪዛ ዕገዳ የህወሓት ምላሽ


TPLF

“ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ በትግራይ ህዝብ ላይ እንደሚፈፀመው ሁሉ በወራሪዎች እየተጠቃ ያለ በመሆኑ ከጨፍጫፊዎች እኩል ሊፈረጅ የሚችልበት ምክንያት ፈፅሞ የለም” ሲል “ድምጺ ወያነ” በሚባለው የድርጅቱ ልሳን የተላለፈው የህወሓት መግለጫ ለዩናይትድ ስቴትስ የቪዛ ማዕቀብ ምላሽ ሰጥቷል።

ከሁሉም አስቀድሞ የጆ ባይደን አስተዳደር “ኤስ አር 97” በሚል “አምባገነን” ባላቸው ኢሳያስ አፈወርቂና “ፋሽስት” ባላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቡድን ላይ ተጨባጭ የሆኑ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማስያዊ የማዕቀብ እርምጃ መውሰድ በመጀመሩ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ አድናቆቱን እንደሚገልፅ አስታውቋል።

“ይሁንና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ቪዛን ስለመከልከል ጉዳይ ባወጡት መግለጫ የህወሐት አባላትንም ይመለከታል ማለቱ ህወሓት በማንኛውም ህዝብም ላይ ህጋዊ አካል ላይ የፈፀመው በደል የለም ብቻ ሳይሆን እሱ ራሱ እንደ ትግራይ ህዝብ ሁሉ ተጠቂና የወረራ ሰለባ መሆኑን የጆ ባይደን አስተዳደር፣ ዓለም አቀፍ ማኅብረሰብ፣ የትግራይ ህዝብ ወዳጆችና ደጋፊዎች ሁሉ ሊያውቁት ይገባል” ይላል ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ ያወጣው መግለጫ። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እርምጃውን በድጋሚ እንዲፈትሽም ህወሓት ጥሪ አሰምቷል።

XS
SM
MD
LG