በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እምቦጭ አረምን ለማስወገድ

በጣና ሐይቅ ላይ እየተስፋፋ ያለውን እምቦጭ አረም ለማስወገድ ኅብረተሠቡ በነቂስ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

ጣና ሀይቅ ለክልሉ፣ ለሀገር ኅልውና ሲሆን “እምቦጭ” የተባለ መጤ አረም አሣዎችን፣ የአዕዋፋት ዝርያዎችን ኅልውና አደጋ ላይ ጥሏል፡፡
በጣና ሀይቅ ዳርቻ የሚበቅሉ ሣሮች፣ ዙሪያውን “እምቦጭ” በተባለው መጤ አረም ተሸፍኗል፡፡
“እምቦጭ” የተባለው መጤ አረም በጣና ላይ የሚገኙ የብዝሃ ህይወትን እያጠፋ ይገኛል፡፡
ከሃያ ሥምንት በላይ የአሣ ዝርያዎች በጣና ውስጥ ይገኛሉ፤ ከእነዚህም ውስጥ ሃያ የሚደርሱት በሌላ ዓለም የሌሉ ናቸው፡፡ በአሣ አስጋሪነት የሚተዳደሩ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቤተሰቦችም ይገኛሉ፡፡
ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶም፣ ከክልሉና ከተለያዩ ሥፍራ የተወጣጡ ማኅበረሰቦች፣ ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ተመራማሪዎች እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG