በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

ዓርብ 28 ሚያዚያ 2017

Calendar

በትግራይ ክልል በሰውና በእንስሳት ያጋጠመ ድርቅ እንደሌለና ለመጭው ክረምት ዝግጅት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የክልሉ የእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ አሳውቋል፡፡

በትግራይ ክልል በሰውና በእንስሳት ያጋጠመ ድርቅ እንደሌለና ለመጭው ክረምት ዝግጅት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የክልሉ የእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ አሳውቋል፡፡ በሌላ በኩል እየተቀያየረ ባለው የተፈጥሮ የአየር ሁኔታ ምክንያት ዘንድሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ላይ የተምች ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል ከወዲሁ ተሰግቷል፡፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ገና ከአሁኑ ታይቷል፡፡

ከዚህም በመነሳት ገበሬዎች ማሣችውን በጥንቃቄ በፈተሽ ያገኙት መረጃ በፍጥነት ለባለሞያዎች ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ማሣሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

በትግራይ ክልል በአለፈው ክረምት ጥሩ ዝናብ በመዝነቡ ምክንያት አርሶ አደሩ ጥሩ ምርት ማግኘቱን የትግራይ ክልል የእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ ግምገማ ይገልፃል፡፡

ገበሬው ከክረምቱ ዝናብ ብቻ ሳይሆን በመስኖ ማልማትን፣ በቂ ውሃ ማግኘት መቻሉንም ቢሮው ያስረዳል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በኤርትራ ተከስቷል ስለተባለው ድርቅ

  • አዳነች ፍሰሀየ

አቶ ተስፋይ ገብረማርያም

በኤርትራ የእርሻ ሚኒስቴር የሰብል ልማት ኃላፊ አቶ ተስፋይ ገብረማርያም ኤርትራ ውስጥ ከድሕረ ነፃነት አንስቶ ድርቅን ለመቋቋም የተለያዩ የውሀ ማቆርና የአፈር መሸርሸር መከላከል ሲደረግ ስለቆየ በአሁኑ ወቅት የሚያሳስብ ሁኔታ የለም ይላሉ።

በኤርትራ የእርሻ ሚኒስቴር የሰብል ልማት ኃላፊ አቶ ተስፋይ ገብረማርያም ኤርትራ ውስጥ ከድሕረ ነፃነት አንስቶ ድርቅን ለመቋቋም የተለያዩ የውሀ ማቆርና የአፈር መሸርሸር መከላከል ሲደረግ ስለቆየ በአሁኑ ወቅት የሚያሳስብ ሁኔታ የለም ይላሉ። አስመራ ያለው ዘጋብያችን ብርሀነ በርሀ ነው አቶ ተስፋይን ያነጋገረው።

በሌላ በኩል ግን በድርቅ የተመቱ በርካታ የኤርትራ አካባቢዎች እንዳሉ በምግብ እጥረት የሚስቃዩ ህፃናትም እንዳሉ ኒዊስ ስቴትመንት የተባለው ለንደን የሚታትም መፅሔት ባወጣው ፁሑፍ አመላክቷል።

ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG