በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዓርብ 31 መጋቢት 2017

Calendar

የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ሜለኒያ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ባዘጋጀው የ2017 ዓ.ም. ዓለምቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ሜለኒያ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ባዘጋጀው የ2017 ዓ.ም. ዓለምቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ሜለኒያ ባለቤታቸው ሥልጣን ከያዙ በኋላ አብዛኛውን ጊዜ የቆዩት ከሕዝብ ዕይታ ውጭ ቢሆንም ባለሞያዎች ግን የርሣቸው ባነስተኛ ደረጃ እንኳ መገኘት በቀጣይ ወራት ተሳትፏቸውን ይበልጥ ለማስፋት ፍላጎት እንዳላቸው ያሳያል ይላሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ አስቀድሞ ሃያ አንድ አሁን መድረክ ራሱን ካገለለ በኋላ የሚያካሂዱት ድርድር ጊዜ እና ዕድል የባከነበት ነው ሲሉ አንድ የቀድሞ የፓርላማ አባል ገለጡ፡፡

የኢህአዴግን ፖሊሲዎች ደግፈው የአካባቢው አስተዳደር አፈፃፀም ነቅፈው ዶ/ር አሸብር ወልደጊወርጊስ የፖለቲካ ድርድሩ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ሊያጠላበት አይገባምም ብለዋል፡፡

ከድርድሩ ሂደት ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ መድረክ በትናንትናው ዕለት ራሱን ያገለለ ሲሆን ስድስት ተቃዋሚ ድርጅቶች አዲስ የመሰረቱት ሌላ ጥምረትም ኢህአዴግ የአደራዳሪ ሚናን አልቀበልም በማለቱ ከድርድሩ ለመውጣት ውይይት እንደሚያደርጉ ገልጠዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ እንዲቀጥል ሕዝቡ ፈቃዱን ሰጥቷል የሚለው የመንግሥት መረጃ ሕዝብን መናቅ ያመነጨው ነው ሲሉ አንድ እውቅ የተቃዋሚ መሪ ነቀፉ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ እንዲቀጥል ሕዝቡ ፈቃዱን ሰጥቷል የሚለው የመንግሥት መረጃ ሕዝብን መናቅ ያመነጨው ነው ሲሉ አንድ እውቅ የተቃዋሚ መሪ ነቀፉ፡፡

የዓዋጁን ዕድሜ ለማራዘም የተሠጡ ምክንያቶች እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ እንደሆነም ገለጽ፡፡ ሌላው የተቃዋሚ ፓርቲ በበኩላቸው ሰሞኑን በገዥው ፓርቲና በመንግሥት የተወሰኑ ውሳኔዎች በሀገሪቱ የፖለቲካ ሕዋ ላይ ከባድ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራሉ ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ለአራት ወራት ተራዘመ

  • እስክንድር ፍሬው

የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ለአራት ወራት እንዲራዘም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ፡፡ የኢትዮጵያ መሪዎች የዓዋጁን መራዘም አስፈላጊ የሚያደርጉ ምክንያቶች እንዳሉ ሲገልፅ ቆይተዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ለአራት ወራት እንዲራዘም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ፡፡ የኢትዮጵያ መሪዎች የዓዋጁን መራዘም አስፈላጊ የሚያደርጉ ምክንያቶች እንዳሉ ሲገልፅ ቆይተዋል፡፡

ለሥድስት ወራት በሥራ ላይ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ለአራት ወራት እንዲራዘም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወሰነው ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ነው፡፡ በዚሁ ስብሰባ ላይ የተገኙት የኮማንድ ፖስቱ ፅ/ቤት ኃላፊና የመከላከያ ሚነስትር ሲራጅ ፌጌሳ ዓዋጅ እንዲራዘም ያስፈለገበትን ምክንያት ማብራራታቸው በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘገባ ተጠቅሷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG