በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኮራሁባችሁ” - ኦባማ ለአፍሪካ ወጣቶች

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በያሊ ስብሰባ ተሣታፊዎች መካከል፤ ሐምሌ 27/2007 ዓ.ም፤ ኦምኒ ሾርሃም ሆቴል፤ ዋሺንግተን ዲሲ
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በያሊ ስብሰባ ተሣታፊዎች መካከል፤ ሐምሌ 27/2007 ዓ.ም፤ ኦምኒ ሾርሃም ሆቴል፤ ዋሺንግተን ዲሲ

በፕሬዚዳንት ኦባማ የተጀመረው የወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች ጅማሮ የማንዴላ ዋሺንግተን ፌሎውሺፕ መርኃግብር ሁለተኛ ዙር ተሣታፊዎች ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለያሊ 2015 ስብሰባ ተሣታፊዎች ንግግር ሲያደርጉ፤ ሐምሌ 27/2007 ዓ.ም፤ ኦምኒ ሾርሃም ሆቴል፤ ዋሺንግተን ዲሲ
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለያሊ 2015 ስብሰባ ተሣታፊዎች ንግግር ሲያደርጉ፤ ሐምሌ 27/2007 ዓ.ም፤ ኦምኒ ሾርሃም ሆቴል፤ ዋሺንግተን ዲሲ

please wait

No media source currently available

0:00 0:14:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በፕሬዚዳንት ኦባማ የተጀመረው የወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች ጅማሮ የማንዴላ ዋሺንግተን ፌሎውሺፕ መርኃግብር ሁለተኛ ዙር ተሣታፊዎች ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

የዘንድሮው መርኃግብር ተሣታፊዎች ለሆኑ 500 የአፍሪካዊያን ወጣት መሪዎች ስብሰባው በተካሄደበት ኦምኒ ሾርሃም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ “በአፍሪካዊያኑ ወጣት መሪዎች ኮርቻለሁ” ብለዋል፡፡

የአህጉሪቱን ወጣቶች ተሰጥዖ በማስተዋላቸው ያ ትውልድ የሚጠቀምባቸውን ግብዓቶች እንዲያገኝ፤ እርስ በራሱ መገናኘት እንዲችል፤ በሲቪል ማኅበረሰቡ፣ በንግዱ፣ በመንግሥት አመራር ሁሉ በንቃት መሣተፍ እንዲችል ይህንን የወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች መርኃግብር የዛሬ ሁለት ዓመት ማስጀመራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለያሊ 2015 ስብሰባ ተሣታፊዎች ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ፤ ሐምሌ 27/2007 ዓ.ም፤ ኦምኒ ሾርሃም ሆቴል፤ ዋሺንግተን ዲሲ
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለያሊ 2015 ስብሰባ ተሣታፊዎች ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ፤ ሐምሌ 27/2007 ዓ.ም፤ ኦምኒ ሾርሃም ሆቴል፤ ዋሺንግተን ዲሲ

አሁን እየተካሄደ ላለው የማንዴላ ዋሺንግተን ፕሮግራም በመላ አፍሪካ 30 ሺህ ወጣቶች መወዳደራቸውን ፕሬዚዳንቱ አመልክተው የተሣታፊዎቹ ቁጥር በሚመጣው ዓመት እጥፍ እንደሚደረግና አንድ ሺህ እንደሚሆንና መርኃግብሩን ሌሎችም ፕሬዚዳንቶች እየተቀበሉ እንዲቀጥሉበት ተቋማዊ ለማድረግ እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ስብሰባ ወቅት ፕሬዚዳንቱ ባደረጉት ንግግርና ተከትሎም በነበረው የጥያቄና መልስ ክፍለጊዜ ከተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ እስከ ጎጂ ልማዶችን እስከመፋለም፤ ለወጣቶች የተሣትፎ መድረኮችን ከመክፈትና ድምፃቸውን ከመስማት እስከ አመራር ብቃትና የአፍሪካን የአዕምሮ ንጥፈት እስከመቋቋምና ገፅታውን እስከመቀየር ያሉ በርካታ ነጥቦች ተነስተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG