ቅዳሜ, የካቲት 13, 2016 የአካባቢው ጊዜ 19:59

  ዜና

  አቶ ግርማ ሠይፉ እና የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ተይዘው ተለቀቁ

  ከተያዙት መካከል አንዱ “እጃቸው ያለመያዝ መብት” ያላቸው እንደራሴ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ግርማ ሠይፉ እንደሆነም ታውቋል፡፡

  አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ
  አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ
  መለስካቸው አምሃ  ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ - የአንድነት ሊቀመንበርዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ - የአንድነት ሊቀመንበር
  x
  ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ - የአንድነት ሊቀመንበር
  ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ - የአንድነት ሊቀመንበር

  አቶ ግርማ ሠይፉ እና የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ተይዘው ተለቀቁ
  አቶ ግርማ ሠይፉ እና የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ተይዘው ተለቀቁi
  || 0:00:00
  ...    
   
  X


  የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር አባላት ዛሬ ለሦስት ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው መለቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

  ከተያዙት መካከል አንዱ “እጃቸው ያለመያዝ መብት” ያላቸው እንደራሴ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ግርማ ሠይፉ እንደሆነም ታውቋል፡፡

  በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት ሌሎች የፓርቲው አመራር አባላት መካከል ሊቀመንበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዋና ፀሐፊው አቶ አሥራት ጣሴ፣ የሥራ አመራር ኮሚቴው አባልና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ዳንኤል ተፈራና ምክትላቸው አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላት አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ስዩም መንገሻ እና አቶ ሺመልስ ሃብቴ፣ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን፤ እንደሁም ሰላሣ ሦስቱ እየተባሉ ከሚጠሩት ስብስብ መካከል የሆኑ ሌሎችም ፓርቲዎች መሪዎች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
  ግርማ ሠይፉ - እንደራሴግርማ ሠይፉ - እንደራሴ
  x
  ግርማ ሠይፉ - እንደራሴ
  ግርማ ሠይፉ - እንደራሴ

  ለአራት ሰዓታት ያህል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የቆዩት የፓርቲው መሪዎች የተለቀቁት በማስጠንቀቂያ ሲሆን ሌሎች የፓርቲው የአዲስ አበባ አባላት የሆኑና ፖስተር ሲበትኑ የነበሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ወጣቶችን በዋስ ለማስለቀቅ እየተጣደፉ እንደነበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

  ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
  ይህ ፎረም ተዘግቷል
  አስተያየቶች
       
  እዚህ ፎረም ላይ የሠፈረ አስተያየት የለም፤ የመጀመሪያው ይሁኑ