በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

29 ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ እግር ኳስ ውድድር እንደቀጠለ ነው።


South Africa African Cup Soccer
South Africa African Cup Soccer
ዓርብ ጥር 17 ቀን 2005 ዓም የ C ምድቦች ተጫውተው ናይጄሪያ ከዛምቢያ አንድ እኩል ሲለያዩ ቡርኪና ፋሶ ኢትዮጵያን 4 ለ ዜሮ አሸንፏል።

በተለይ የኢትዮጵያና ቡርኪና ፋሶ ጠዋታ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ስለነበር፥ ቀጣዩን አጠር ያለ ዘገባ እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ ቡድን ጨዋታው በተጀመረ ገና በ 5ኛው ደቂቃ ላይ ፍፁም ያለቀላት ጎል አግኝቶ ሳይጠቀምባት መቅረቱ ብዙዎችን ያሳዘነ ነበር። ሳላዲን ሰዒድ አመቻችቶ ያሳለፈለትን ኳስ መሃል አጥቂው ሽመልስ በቀለ በረኛውን ለብቻው አገኘና ወደ ጎል የመታት ኳስ ማዕዘን መትታ ተመለሰችበት። ይህ አልበቃ ብሎ ግብ አዳኙ አዳነ ግርማ 10ኛው ደቂቃ ላይ ጉዳት ደርሶበት ወጣ። ቡድኑን በጣም እንዳጎደለ ግልጽ ሆነ።

ጨዋታው ቀጥሎ እያለ ዋሊያዎች በርቀት ያሸጋገሯትን ኳስ የቡርኪና በረኛ አብዱላዬ ሡላማ ከፍፁም ቅጣት ክልል ውጭ ሆን ብሎ ወጥቶ በመያዙ ዳኛው በቀይ ካርድ ከሜዳ አባረሩት። ቡርኪናዎች በአሥር ተጫዋቾች ብቻ ቀጠሉና፥ ወዲያው በጠቅላላው ሁለት ጎሎችን ባስገኘላቸው ፈጣን አጥቂ አሌን ትራኦሬ ተካሱ። ሌሎች ሁለት ጎሎች በዘጠናውና በባከነ ተጨማሪ ሰባት ደቂቃ አከሉና ጨዋታው በቡርኪና ፋሶ 4 ለ 0 አሸናፊነት ተፈጸመ።

በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ፥ ቡርኪና ፋሶ ከዛምቢያ ይጋጠማሉ።
XS
SM
MD
LG