በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥታቸው ቆርጧል አሉ


የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባርናባ ማሪየል ቤንጃሚን
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባርናባ ማሪየል ቤንጃሚን

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት መንግሥታቸው በስምምነቱ በተጥቀሰው መሰረት ሃይሎቹን ከመዲናዋ ከጁባ ማስወጣት መጀመሩን ይፋ ባደረገበት በትናናንትናው ዕለት ነው።

የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መንግሥታቸው ባለፈው ነሃሴ ወር በቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪያክ ማቻር በሚመሩት ኣማጽያን እና በፕረዚደንት ሳልቫ ኪር መንግሥት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነቱ እንደጸና ነው ሲሉ በድጋሚ ተናገሩ።

የመንግሥታቸውን ለሰላም ውሉ ቁርጠኝነት የገለጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባርናባ ማሪየል ቤንጃሚን ዓለም ኣቀፉ ማህበረሰብም ቢሆን ለሰላም ውሉ ተግባራዊነት ሊሰጥ የገባውን የሎጂስቲክስ ድጋፍ በተግባር መተርጎም ያለበት ወቅት አሁን ነው ብለዋል።

“እንደምታውቁት ፕሬዚደንታችን ሳልቫ ኪር ማያርዲት ውሉን እንደፈረሙ ወዲያውኑ ዘላቂ ተኩስ ኣቁም ኣወጅን፡ የጦር ሰራዊት ኣዛዦቻችንም ሰራዊቱን በሃያ ኣምስት ኪሎ ሜትር ከጁባ ኣውጥተው እንዲያሰፍሩ መመሪያ ሰጠን። በዚያ መሰረትም እነሆ ዛሬወታደሮቹን ወደተመደበው ስፍራ ማንቀሳቀስ ተጀምሩዋል።”

የደቡብ ሱዳን መንግስት የሰላም ውሉ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ለሃገሩ ህዝብና ለዓለም ኣቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል ብለዋል ። እኤኣ ነሃሴ ሃያ ስድስት የተፈረመው የሰላም ውል አማጽያኑና መንግስቱ ለሰላሳ ወራት በጋራ ስልጣን እያስተዳደሩ ለሰላሳ ወራት ቆይተው ከዚያም በ2018 ምርጫ እንዲካሄድ ያሳስባል።

ኣማጽያኑ ቀዳሚ መልእክተኛ ቡድናቸውን ወደጁባ እንዲልኩ እንጠብቃለን ሲሉም አክለዋል።። ውሉ ከተፈረመበት እለት በሁዋላ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ሁሉም ወታደራዊ ሃይሎች በኣስራ ኣምስት ማይል ርቀት እንዲርቁ ያሳስባል። ያ የጊዜ ገደብ በዚህ ሳምንት ሲሆን ያልተከበረ እንደሆን ተጠያቂ የሚሆኑት ኣማጽያኑና ኢጋድ ይሆናሉ ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

በደቡብ ሱዳንዋ መዲና ትናንት ሰኞ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የምስራቅ ኣፍሪካ ሀገሮች የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን ኢጋድ መሪዎች ጉባዔ ለሌላ ጊዜ ተላልፉዋል።

የስብሰባው አላማ ስለሰላም ውሉ ገቢራዊነት ለመነጋገር፡ ተፋላሚዎቹን ወገኖች ለማበረታት እና ጦርነቱ ማክተሙን በይፋ ለማወጅ መሆኑ ተገልጹዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቤንጃሚን እንዳሉት ጉባዔው የተላለፈው በኢጋድ መሪዎች ጥያቄ ነው። የኣሜሪካ ድምጹ ጄምስ በቲ ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጂት ታዬ አቅርባዋለች ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥታቸው ቁርጥ ነው አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:37 0:00
VOA60 Africa- South Sudanese army begings withdrawing from Juba
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:00 0:00

XS
SM
MD
LG