Last updated at: 26.12.2012 00:28

“ስወድሽ” - ሚካኤል በላይነህና ገብረ ክርስቶስ ደስታ
ምርጥ ሥዕሎቹና የግጥም ሥራዎቹ ዘመን ተሻግረው ዛሬም የአያሌ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን የኪነ-ጥበብ አድናቂዎችን ቀልብ እንደሳቡ ነው፤ ሠዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ።

የጥበብ አዋቂዎች በታላቅ አድናቆትና አክብሮት የሚያወሱት ይህ ሠው በህይወት ካለፈ ሦሥት አሥርታት ቢቆጠሩም፥ “ስወድሽ-ስወድሽ’ን” የመሳሰሉ ውብ ህያው ሥራዎቹ እንደ አዲስ ነፍስ ዘርተውና ገዝፈው በሌላ ግሩም ሥልት ተቀምመው በጆሯችን መንቆርቆር ከበቁ ምናልባትም ቀዳሚ እንጂ የመጨረሻ ከማይሆኑ ሥራዎቹ ውስጥ ናቸው።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በቅርቡ «ናፍቆት፤» በሚል ርዕስ ለአድማጭ ጆሮ ባበቃው አዲስ ሲዲው በተካተተችው “ስወድሽ” ዙሪያ እናወጋለን።

ከሚካኤል በላይነህ ጋር ያደረግነውን ወግ ከዚህ ያድምጡ።

“ስወድሽ” - ሚካኤል በላይነህና ገብረ ክርስቶስ ደስታ

<link rel="canonical" href="http://amharic.voanews.com/content/michael-belayneh-gebre-kirstos-siwodish-12-23-12/1572119.html"/><meta name="syndication-source" content="http://amharic.voanews.com/content/michael-belayneh-gebre-kirstos-siwodish-12-23-12/1572119.html"/>
Copy to clipboard Close