በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ስደተኞችን ወደ አገር መለሰ


የኢትዮጵያ ስደተኞች በካኩማ ካምፕ
የኢትዮጵያ ስደተኞች በካኩማ ካምፕ

በሕገ ወጥ መንገድ የኬንያን ድምበር ተሻግራችሁዋል በመባል የተከሰሱ ከ28 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን ኦሮሞ ስደተኞች ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ የማርሳቢት ፍርድ ቤት መወሰኑ ታዉቋል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ስደተኞቹ ጥገኝነት እንዲያገኙ ለኬንያ መንግስት ያቀረበዉ ጥያቄ አንድ ስደተኛ ከማስጠልል በስተቀር ተቀባይነት እንዳላገኘ ተናግሯል። እንዲመሰሱ የተደረጉት ስደተኞች ግን አሁን ያሉበት ሁኔታ አልታወቀም።

ስደተኞቹ ከሁለት ሳምንታት በፊት በሰሜኑ ኬንያ ማርሳቢት ግዛት በፖሊስ ቁጥጥር በዋሉበት ግዜ ጉዳያቸዉ በአግባቡ እንዲታይ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ኬንያ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት፣ የኬንያ መንግስትን መጠየቁ የሚታወስ ነዉ።

ነገር ግን ከስደተኞቹ አብዛኛዎቹ ኬንያ ዉስጥ ጥገኝነት ማግኘት ለደህንነታቸዉ ያሰጋል በማለት ኬንያ ዉስጥ ጥገኝነት ስላልፈለጉና ወደ ሌላ አገር የመሻገር ፍላጎት ስላሳዮ ፍርድ ቤቱ ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ አዟል ሲሉ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ኬንያ ቅርንጫፍ ቃል አቀባይ ዱክ ምዋንቻ ተናግረዋል።

በፍርድ ሂደቱ ወቅት የስደተኞቹን መብት ለማስጠበቅም ድርጅቱ ጠበቆችን ወደ ማርሳቢት ልኮ የነበረ ሲሆን ወደ 28 ከምሆኑ ኢትዮጵያዉያን አንድ ሰዉ ብቻ የጥገኝነት ጥያቄ በማቅረቡ ሌሎች እንዲመለሱ ተወስኗል ሲሉ ቃል አቀባዩ አብራርተዋል። የጥገኝነት መብቱ ተጠበቀለት የተባለዉም ኢትዮጵያዊ በቅርቡ ወደ ናይሮቢ እንደሚወሰድና እንደሚመዘገብም አክሎ ተናግረዋል።

ካኩማ የስደተኞች ካምፕ በኬንያ
ካኩማ የስደተኞች ካምፕ በኬንያ

በምኅፃሃረ ቃሉ ዲአርኤ (DRA) በመባል የምታወቀዉ የኬንያ ስደተኞች ጉዳይ ቢሮም በበኩሉ ስደተኞቹ እንዲመለሱ መደረግ እዉነት መሆኑን ተናግረዋል። ከቢሮዉ ባገኘን መረጃም መጀመርያ የስደተኞችን ምዝገባ የምያካሂድ ስደተኞቹ የተያዙበት ግዛት ሲሆን፣ ከዚያ በኋላም ቢሮዉ ስደተኞቹን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድና ወደሚገባቸዉ ቦታ እንደሚወድ ስማቸዉ እንዳጠቀስ የጠየቁ የኬንያ ስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ባልደረባ ገልጸዉልናል።

አሰራሩ ጥገኝነት ፈላጊዎችን ከድንበር እንዲመለሱ በማድረግ ለአደጋ አያጋልጥም ወይ በማለት ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ይህ ችግር እንዳይከሰት መስሪያ ቤቱ በድምበር አካባቢ ለሚገኙ ፖሊሶች በስደተኞች አያያዝ ዙርያ ስልጠና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጸዉልናል።

ዳዊት ገልሞ ከናይሮቢ ያደረሰንን ዘገባ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

የኬንያ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ስደተኞችን ወደ አገር መለሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:28 0:00

XS
SM
MD
LG