በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያዊያኑ የትዊተር ዘመቻ ወደ ኦባማ #EthiopiansMessageToObama


ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማበትዊተር ለመጀመሪ ጊዜ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ፣ @POTUS, May 28, 2015(ግንቦት 20/2007 ዓ.ም)ፕሬዚዳንቱ እስከዚያ የትዊተር አካውንት አልነበራቸውም፡፡
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማበትዊተር ለመጀመሪ ጊዜ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ፣ @POTUS, May 28, 2015(ግንቦት 20/2007 ዓ.ም)ፕሬዚዳንቱ እስከዚያ የትዊተር አካውንት አልነበራቸውም፡፡

የፌስቡክ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ኢትዮጵያ ሊሄድ መሆኑ ተሰማ፡፡

የኢትዮጵያዊያኑ የትዊተር ዘመቻ ወደ ኦባማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:25 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የትዊተር ዘመቻ፡- #EthiopiansMessageToObama (የኢትዮጵያዊያን መልዕክት ለኦባማ) የቴሌቪዥን ፕሮግራሙን የትዊተር ማጨናነቁ ተዘግቧል፡፡

“ቮካቲቭ ዶት ኮም” የሚባል የኢንተርኔት ብዝኃሚድያ ባወጣው ዘገባ ፕሬዚዳንት ኦባማ ማክሰኞ፤ ሐምሌ 14/2007 ዓ.ም በኮመዲ ሴንትራሉ “ ዘ ዴይሊ ሾው” አቅራቢ ጆን ስቴዋርት የስንብት ፕሮግራም ላይ ቀርበው ነበር፡፡

ያኔ “ኢትዮጵያዊያኑ የትዊተር ማዕበል በጣቢያው ላይ ለቅቀው ሰሞኑን ኢትዮጵያን የሚጎበኙትን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትኩረት ለማግኘት ጥረዋል” ብሏል ዘገባው፡፡

የኢትዮጵያዊያኑ በተጠቀሙበት ሃሽታግ ወይም መነጋገሪያ#EthiopiansMessageToObama የትዊተር ዘመቻው ያተኮረው ፕሬዚዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ወቅት ለሰብዓዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጡ መጠየቅ ነበር፡፡ መልዕክቶቹ ፀሐፊዎቹ የኢትዮጵያ መንግሥት እየፈፀማቸው ናቸው ያሏቸውን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችም የሚዘረዝሩ እንደነበሩ ተዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያዊያኑ መነጋገሪያ ወይንም ሃሽታግ #EthiopiansMessageToObama ያስነሳውን "የትዊተር ማዕበል" ከዚህ በታች ይከታተሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ የፌስቡክ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ኢትዮጵያ ሊሄድ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ማርክ ዙከርበርግ
ማርክ ዙከርበርግ

ማርክ ዙከርበርግ ወደ ኢትዮጵያ ለምን እንደሚሄድ እና ለምን ከፕሬዚዳንቱ ጋር እንደሚሄድ ለማጣራት እየጣርን ነው፡፡

አሪየል ነኝ ያሉ ለፌስ ቡክ ለተላከ ጥያቄ መልስ የሰጡ ሰው ግን “ማርክ አይሄድም፤ ኬንያ ውስጥ በሚካሄደው ዓለምአቀፍ የሥራ ፈጠራ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ግን የፌስ ቡክ የግንኙነቶች ኃላፊ ክሪስ ዳንኤልስ ይሄዳል” ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ አቋም የተቃዋሚ አባላትና የሲቪል ማኅበረሰቡ እሴቶችን፤ እንዲሁም የሕዝቡንም ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት መብቶች ማክበር መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ኪርቢ ይህንን መግለጫ የሰጡት “የኢትዮጵያ መንግሥት የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ለመቀበል እየተዘጋጀ እንኳን የተቃዋሚ መሪዎችን እያሠረ ነው” ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG