በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታንዛንያ ፖሊስ 44 "ህገ-ወጥ" የተባሉ የኢትዮጵያ ፍልሰተኞችን በቁጥጥር ሥር አውሏል


ፋይል ፎቶ - አፍሪካውያን ፍልሰተኞች በደቡብ አፍሪካ ድንበር ላይ
ፋይል ፎቶ - አፍሪካውያን ፍልሰተኞች በደቡብ አፍሪካ ድንበር ላይ

የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ጉዳይ በታንዛንያ እስር ቤት።

የታንዛንያ ፖሊስ ቁጥራቸዉ 44 የሚሆኑና "ህገ-ወጥ" የተባሉ የኢትዮጵያ ፍልሰተኞችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።

ፍልሰተኞቹ የተያዙት በሰሜን ምሥራቅ የሃገሪቱ ግዛት ታንጋ በመባል በምጠራ ሥፍራ ሲሆን በቁጥጥር በዋሉበት ግዜም ፍልሰተኞቹ ተጠይቀው እንደተናገሩት ዓላማቸዉ ወደ ሃገሪቱ ዋና ከተማ ዳረኤ ሰላም ለማምራት እንደነበር ተናግረዋል።

ከፍልሰተኞቹ አንዱ የሆነዉ ሰለሞን ፍቅሩ የተባለ ኢትዮጵያዊ እንደ ተናገረዉ መነሻቸዉ የኢትዮ-ኬንያ የድምበር ከተማ የሆነችዉ ሞያሌ እንደነበረና ሥራ ለመፈለግ ወደ ታንዛንያ እንደመጡም ተናግረዋል።

የአካባቢዉ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሚስኬይላ ምስሃዮ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩ ፍልሰተኞቹ በተያዙበት ወክት በሸራ በተሸፈነ የጭነት መኪና ዉስጥ እንደነበሩ ተናግረዋል።

ገልሞ ዳዊት ያጠናቀረውን ዘገባ ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

የታንዛንያ ፖሊስ 44 "ህገ-ወጥ"  የተባሉ የኢትዮጵያ ፍልሰተኞችን በቁጥጥር ሥር አውሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG