በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ኀዘን ላይ ነች


ኢትዮጵያ ኀዘን ላይ ነች
ኢትዮጵያ ኀዘን ላይ ነች

please wait

No media source currently available

0:00 0:42:02 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የእሥልምና መንግሥት ነኝ በሚለው የሽብር ቡድን ሊብያ ውስጥ 29 ኢትዮጵያዊያንና አንድ ኤርትራዊ መገደላቸውን ኢትዮጵያዊያንና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እያወገዙ ነው፡፡

ግድያውን ለማውገዝ ዛሬ - ማክሰኞ ሚያዝያ 13/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የከተማይቱ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ሰላማዊ ሠልፍ አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በፍልሰተኞቹና በስደተኞች ዜጎቹ ግድያ ላይ አስቀድመው የሰጧቸውን አስተያየቶችም ወቅሰዋል።

የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም መንግሥት ሙሉ ወጭውን ሸፍኖ ዜጎቹን ከአደጋ ለመታደግ እንደሚንቀሳቀስ አስታውቀው በፈቃዳቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከነገ - ረቡዕ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ጀምሮ ያሉት ሦስት ቀናት ብሔራዊ የኀዘን ቀናት እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ፓርላማ ወስኗል፡፡

በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና በውጭ ሃገሮች በሚገኙ የኢትዮጵያ ተቋማት ሁሉ የሃገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብም ፓርላማው በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ “በዚህ ወቅት በአንድ ልብ፣ በአንድ ሃሣብ መቆም አለብን ሲሉ” ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሊብያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን ላይ የተፈፀመውን ግድያ አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠርባቸው በሚችሉ አካባቢዎች ያሉ ዜጎች በፈቃዳቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የመንግሥታቸው ፍላጎት እንደሆነም ገልፀዋል።

ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ደግሞ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን በቅርቡ በደቡብ አፍሪቃ፣ በኢትዮጵያዊያንና በሌሎች ሃገሮች ስደተኞች ላይ የደረሰውን ግፍና በደል በመቃወም ትላንት - ሰኞ ሚያዝያ 12/2007 ዓ.ም በአሜሪካ ደቡብ አፍሪቃ ኤምባሲ ደጃፍ ተገኝተው ድምፃቸውን አሰምተዋል።

በሰልፉ ላይ ቁጥሩ የበዛ ሰው መገኘቱ ተዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል ግን ሊብያ ውስጥ ያለው ሁኔታ አሁንም እጅግ አሳሳቢ መሆኑንና ዛሬ፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 13/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ትሪፖሊ ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ከመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊታቸውን በሸፈኑ ሰዎች ታፍሰው መወሰዳቸውን አንድ እዚያው አካባቢ ተደብቄ ነው ያለሁት ያሉ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

“እዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ክርስቲያን ወገኖቻቸውን ከጥቃት ለመታደግ ሕይወታቸውን አሳልፈው ለአደጋ እየሰጡ እየተከላከሉልን ነው” ሲሉም እኒሁ ስደተኛ ተናግረዋል፡፡

በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሣደር ማኅሙድ ድሪርም ኤምባሲው እያደረገ ስላለው ጥረት ለቪኦኤ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለተሟሉ ዘገባዎቹና መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG