በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ 2007፡- ምርጫ ቦርድ ከአንድነት፣ ሰማያዊና መኢአድ ጋር ውዝግብ ገብቷል


ታህሳስ 28 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለአንድነትና መኢዐድ በጻፈው ደብዳቤ} ሁለቱ ፓርቲዎች ያከናወኑት የአመራር ምርጫ በፓርቲዎቹ መተዳደሪያ ደምብ መሰረት አልተከናወነም ሲል፤ የውስጥ አሰራሩን እንዲያሻሽል ጠይቋል።

ይህንን ተከትሎ አንድነትና መኢዐድ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት የአመራር ምርጫ አካሂደዋል። አንድነት አቶ በላይ በፈቃዱ በፕሬዝደንትነት ሲመርጥ፤ መኢዐድ አቶ ማሙሸት አማረን የፓርቲው መሪ አድርጎ መርጧል። አቶ አበባው ማህሪ በዚህ ጉባዔ አልተሳተፉም።

ምርጫ ቦርድ በዚህ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አልተገኘም። የምርጫ ቦርድ ለቪኦኤ በሰጠው ቃል በጠቅላላ ጉባዔው ምን እንደተሳተፈ አናውቅም ብለዋል። ምርጫ ቦርድ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ ተጨማሪ የሁለት ሳምንት የጊዜ ወሰን ሰጥቷል።

ለጥያቄዎ መልስ ዝግጅት በምርጫ 2007 ተፎካካሪ ፓርቲዎችና፤ የምርጫ ቦርድ ሚናና ሃላፊነቶች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት አሰናድቷል።

XS
SM
MD
LG