በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲሞክራሲ በተግባር!


”የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስትና የሰብአዊ መብቶች ከበሬታ” ዛሬ ተከብሮ የዋለውን የአለም ሰብአዊ መብቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ለዲሞክራሲ በተግባር ፕሮግራም የመረጥነው ርእስ ነው።

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከነሐሴ 15 ቀን 1987 አም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ ውሏል የተባለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገ-መንግስት ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በተመለከተ አንቀጽ 10 ቁጥር አንድና ሁለት እንዲህ ይላል።

ሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ፥ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው።

የዜጎችና የሕዝቦች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ ይላል።

የሀገሪቱ የበላይ ሕግ፥ ሕገ-መንግስቱ መሆኑ በግልጽና ጥርት ባለ ቋንቋ ሰፍሯል። እውን ግን ህጉ ተግባራዊ ሆኗል?

የሕግ ባለሞያው የሆኑትን አቶ ተማም አባቡልጉን አነጋግረናል።

XS
SM
MD
LG