በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናትድ ስቴትስ ዲሞክራቲክ ፕሬዚደንታዊ ተወዳዳሪዎች መካከል የተካሄደ ክርክር


ሁለቱ የዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዚደንታዊ ተወዳዳሪዎች በኒው ሃምፕሸሩ ክርክር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ። የሁለቱ ክርክር ትናንት የተካሄደው የመጀመሪያው ፕሬዚደንታዊ ፕራይመሪ ከመደረጉ ከቀናት አስቀድሞ ነው።

የቀድሞዋ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተንና የቬርሞንቱ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ የተጋጋለ ክርክር ያካሄዱት፣ መካከለኛ ገቢ ያላቸውን አሜሪካውያንን በመርዳት ረገድ ማንኛቸው የተሻሉ እንደሆኑ ለማሳመን ባደረጉት ጥረት ነው።

የተለመደው የእጅ ሰላምታ ልውውጥ ተካሂዶ ብዙም አልቆየ፣ በሁለቱ መካከል አቧራ ያስነሳ ክርክር የቀጠለው። "መናገር ያለብዎት ነገር ካለ በቀጥታ ይናገሩት እንጂ፣ ባገኘሁት እርዳታ ምክንያት የአመለካከት ይሁን የድምፅ ለውጥ ለማድረጌ ምንም ማረጋገጫ የለዎትም። የማያወላውል አቋም ያለኝ፣ በወከለኝ ወገን በኩልም እስከማውቀው ድረስ የታመንኩ ነኝ። በዚህ ደግሞ ኩራት ይሰማኛል። ስለዚህ እርስዎም ሆኑ ለምርጫ ቅስቀሳ የሚያደርግልዎ ክፍል፣ ይሄን የጀመራችሁትን አሽሙር አቁማችሁ በዋናው የአር ጉዳይ ላይ እንነጋገር።"የቀድሞዋ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን ብለዋል።

በውጪ ጉዳዮች እረገድ ሂላሪ የተሻለ ልምድ እንዳላቸው ያመኑላቸው ሴናተር በርኒ ሳንደርስ የውሳኔ አሰጣጣቸውን ግን ጥያቄ ውስጥ ያስገባሉ።

"ልምድ ብቻ አይደለም ዋናው ቁም-ነገር፤ ውሳኔ አሰጣጥም ትልቅ ቦታ አለው። ከሴናተር ኦባማ ጋር እንዲሁ ለፕሬዚደንትነት በገጠሙበት ወቅት፣ ኦባማ ከጠላቶቻችን ጋርም መወያየት ጠቃሚነት አለው በማለታቸው የዋህና ገራገር አድርገው ነበር የሞገቷቸው። እንደሚመስለኝ ግን፣ እንደነዚያ ካሉት ጋር ነው መወያትም ሆነ መደራደር ያለብን።" ብለዋል ሴናተር በርኒ ሳንደርስ።

ሁለቱ ዲሞክራቶች፣ በምርጫ ዘመቻው ተራማጅ ሃሳብ ያለው ማነው በሚለው ነጥብ ዙሪያም ተከራክረዋል። ከኒው ሃምፕሸሩ ክርክር በፊት በተካሄደ የሕዝብ አስተያየት መለኪያ መሠረት፣ ሂለሪ ክሊንተን፣ ከሴናተር ሳንደርስ በ16 ነጥብ ወደ ኋላ እንደነበሩም በመርዳት ረገድ ማንኛቸው የተሻሉ እንደሆኑ ለማሳመን ባደረጉት ጥረት ነው። ዘገባውን ለማዳመት የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

በዩናትድ ስቴትስ ዲሞክራቲክ ፕሬዚደንታዊ ተወዳዳሪዎች መካከል የተካሄደ ክርክር
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:24 0:00

XS
SM
MD
LG