በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡሩንዲ መንግስት ብሄራዊ ውይይት ለማካሄድ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ


የቡሩንዲ መንግስት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ከመላ የሀገሪቱ ህዝብ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆነ አስታውቋል። መንግስት ይህን ያለው በምስራቅ አፍሪቃ ማህበረሰብ አስተባባሪነትና በኡጋንዳው ፕረዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ሸምጋይነት ከሚመለከተው የሀገሪቱ ህዝብ ጋር አካታች የሆነ ውይይት እንዲካሄድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአፍሪቃ ህብረት ባለፈው ሳምናት ጥሪ ካደረጉ በኋላ ነው።

የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አለይን ንያሚትዌ፣ ንግግሩ የሚካሄደው በአሩሻው ስምምነት መንፈስ ብቻ ሳይሆን በቡሩንዲ ሪፑብሊክ ህገ-መንግስት መሰረት ነው ብለዋል። በህገ-መንግስቱ መሰረት ህዝባዊ ውይይቱን በሀላፊነት የሚያቀናጁ ተቋማት እንደተመሰረቱም አክለው ገልጸዋል።

ካለፈው አርብ አንስቶ በመዲናይቱ ቡጁምቡራ በፓርቲዎች መካከል ንግግር እንደተጀመረም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ (United States) ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ለቡሩንዲ ወታደራዊ ሃይልና ህዝብ መልእክት አተላላልፈዋል።

“የቡሩንዲ ወታደራዊ ሃይል ሀገሪቱ ከመከፋፈል ወጥታ ለመተባበር ያላትን ብቃት ትወክላላችሁ። ከቡሩንዲ አብራክ የወጣችሁ ልጆችዋ ናችሁ። በአፍሪቃ ዙርያ ሰላም እንዲኖር ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ረድታችኋል። አሁን ደግሞ ከፖለቲካዊ ግጭቶርቃችሁ የሀገሪቱን ህዝብ በመጠበቅ የሀገራችሁን ሰላም በማስከበር ተግባር ጥረት ልትረዱ ትችላላችሁ።” ፕረዚዳንት ኦባማ ለሀገሪቱ ህዝብም ንግግር አድርገዋል።

“የቡሩንዲ ህዝብ ሆይ ዛሬ በቀጥታ ለናንተ ለመነገር የምፈልገው ነገር አለ። ቡሩንዲ ኩሩና ውብ ሀገር ናት። ይሁንና ከቅርብ ወራት ወዲህ የምትወድዋት ሀገር መጻኢ እድል አደጋ ላይ ወድቋል። መሪዎች የጥላቻ ልፈፋ እያሰሙ ናቸው። ዘግናኝ የሆነ የሀይል ተጠቃሚነት ተግባር የንጹሃን ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆችን ህይውትይ አጥፍቷል። ካለፈው የቡሩንዲ አሳዛኝ ታሪክ በመነሳት እንዲህ አይነቱ ግጭት ወዴት ሊያመራ እንደሚችል እንገነዘባለን። መላ የቡሩንዲ ህዝብ ሆይ በህብረት ስትቆሙ የት ልትደርሱ እንደምትችሉ አትዘንጉ። ከቅኝ ተገዥነት ወጥታችሁ እንዴት ሀገራችሁን እንደገነባችሁ ከእርስ በስር ጦርነት ወጥታችሁ ሀገራችሁን መልሳችሁ ገንብታችሁ በሰላም መኖር የተሻለ መሆኑን አይታችኅዋል። የፖለቲካ ተቀናቃኝነትና የጥላቻ ልፈፋ ይህን እድላችሁን እንዲነጥቁ መፍቀድ የለባችሁም።”

ቡሩንዲ ውስጥ ቀውስ የተከሰተው የሀገሪቱ ፕረዚዳንት ፕየር ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር በወሰኑበት ወቅት ነው። ቢያንስ 240 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። በሀገሪቱ ያሉት ተቃዋሚዎች የፕረዚዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ ስልጣን ላይ ለመቆየት መወዳደር የሀገሪቱን ህገ-መንግስት ይጥሳል በሚል ተቃውሞ ማካሄድ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ከ 200,000 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከሀገሪቱ ለመሰደድ ተገደዋል።

የቡሩንዲን በዘር ላይ የተመሰረተ ግጭትን ለማቆም የተደረገው የአሩሻ ውል በሀገሪቱ ምክር ቤት 60 ከመቶ መቀመጫ የሚይዙት ብዙሃኑ ሁቱዎች 40 ከመቶውን መቀመጫ ደግሞ፣ ውሁድኑ ቱትሲዎች እንዲይዙት ይደነግጋል።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለሚካሄዱት ውይይቶች ሲናገሩ ውይይቱ በምን ላይ እንደሚያተኩር አልገለጹም። እሱን የሚወስነው የቡሩንዲ ህዝብ ነው ብለዋል።

የአፍሪቃ ህብረት የሰላምና የጸጥታ መማክርት ቡሩንዲ ውስጥ ያለው ያፖለቲካ ሁኔታ አጣብቂኝ ውስጥ መግባት የጸጥታ ጉድለትና ግጭት “በጥብቅ እንዳሳሰበው የሚገልጽ ዘገባ ባለፈው አርብ አውጥቷል። ነው። የእንግሊዘኛው ክፍል ባልደረባችን ጀምስ ባቲ ያቀናበረውን ዘገባ አዳነች ፍሰህየ ታቀርበዋለች ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የቡሩንዲ መንግስት ብሄራዊ ውይይት ለማካሄድ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:59 0:00

XS
SM
MD
LG