በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


Lucy fossil / 露西化石原貌(美国之音国符拍摄)
Lucy fossil / 露西化石原貌(美国之音国符拍摄)

አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ሉሲ ወይም ድንቅነሽ ከትገኘት አርባ አመት ሞላት፣ ዴንማርክ ለኤርትራውያን የጅምላ ጥገኝነት እንደማትሰጥ አስታወቀች፣ ሲራልዮን ውስጥ የኢቦላ መከላከያ ልብስ እጥረት ተፈጠረ የሚሉትን ርእሶች ነው ዛሬ የምንመለከተው።

History Channel የተባለ ስለታሪክ የሚግልጽ የአሜሪካ ቴሌቪዥን ስርጭት ድረ-ገጽ ዝነኛዋ “ሉሲ” ወይም ድንቅ ነሽ ስለተገኘችበት አርባኛ አመት ጽሁፍ አቅርቧል።

የሰው ልጅ አመጣጥ ታሪክ ተመራማሪ Donald Johnson እና የድህረ-ምረቃ ተማሪ Tom Gray ከአርባ አመታት በፊት በኢትዮጵያው የአፋር ክልል የቅድመ-ሰው ቅሪት አካላት ፍለጋ ሲዘዋወሩ ባለፈው ማክሰኞ በዋለው እአአ ህዳር 24 ቀን 1974 አም. አንድ ነገር አደናቀፋቸው። የ ያደናቀፋቸው ነገርም ከዚያ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የዝንጀሮ አምሳያ ያለው የቅሬት አካል ክፍል ነበር።

ያቅሪት አካል ታድያ ውሎ አድሮ የ 3.2 ሚልዮን አመት እድሜ ያላት ”Australopithecus afarensis” የተባለች ከቅድመ-ሰው የዘር ግንድ አንዷ እንደሆነች ለማወቅ ተቻለ ይላል ሂስትሪ ጽረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ። ሉሲ የተገኝበት ሐዳር ክፍል የጥንት ቅድመ ሰው ቅሬት አካል በብዛት የሚኝበት አከባቢ ነው። ሌሎች ርእሶችም አሉንና ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:01 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG