ቅዳሜ, የካቲት 13, 2016 የአካባቢው ጊዜ 03:21

  ኢትዮጵያ በጋዜጦች

  Ethiopian Jews Settle Into Life in IsraelEthiopian Jews Settle Into Life in Israel
  x
  Ethiopian Jews Settle Into Life in Israel
  Ethiopian Jews Settle Into Life in Israel
  አዳነች ፍሰሀየ

   ሎስ አንጀለስ ጋዜጣ ላይ በወጣው ዘገባ መሰረት ለኢትዮጵያውያን አይሁዶች ይሰጥ በነበረው የወሊድ ቁጥጥር መድሀኒት ምክንያት የተከሰተውን ቅሌት መሰረት በማድረግ የእስራኤል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር Depo-Provera ስለተባለው መርፌ  አጠቃቀም ላይ አዲስ መመርያ አውጥቷል።

  የእስራኤል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዋና ስራ አስኪያጅ Ron Gamzu
  የስነ-ተዋልዶ ሀኮሞች የህክምናው አይነት ስለሚያስከትለው ነገር በሚገባ ላልተገነዘቡ ሰዎች ሲሰጥዋቸው የቆዩትን መድሀኒት እንዲያድሱ መመርያ ሰጥተዋል።

  የሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ይህን መመርያ ለማውጣት የተገደደው Gale Gabbay የተባለች እስራኤላዊት ጋዜጣኛ ኢትዮጵያውያኑ ወደ እስራኤል ለመጓዝ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰፈር ላይ ሆነው ይጠባበቁ  ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ ስለ መድሃኒቱ ምንነት ምንም አይነት ማብራርያ ሳይሰጣቸው ወደ እስራኤል ለመሄድ የሚያስፈልጋቸው መድሀኒት የሚል እምነት እንያድርባቸው ተድርጓል የሚል ጽሁፍ ካቀረበች በኋላ ነው ይላል የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ድረ-ገጽ።

  በሌላ ዜና ደግሞ የአርኪዮሎጂ ማለት የጥንት ባህል ጥናትና ምርምር ጠበብት ከአንድ ነጥብ 75 ሚልዮን አመታት በፊት የተሰሩ በጥንታዊነታቸው ቀዳሚ የሆኑ ከዲንጋይ የተሰሩ መጥረብያዎችን በኢትዮጵያ ምድር እንዳገኙ LiveScience የተባለው መጽሄት ድረ-ገጽ ዘግቧል። የጥንት መሳርያዎቹ በኢትዮጵያ ምድር የተገኙት ባለፉት ሁለት አስርተ-አመታት ውስጥ ነው።
  ይህ ፎረም ተዘግቷል
  አስተያየቶች
       
  እዚህ ፎረም ላይ የሠፈረ አስተያየት የለም፤ የመጀመሪያው ይሁኑ