ረቡዕ, ሚያዚያ 01, 2015 የአካባቢው ጊዜ 13:35

የአፍሪካ ቀንድ

አዲሶቹ የኢትዮጵያ ካቢኔ የስራ ዘርፎች

Ethiopia mapEthiopia map
x
Ethiopia map
Ethiopia map
አዳነች ፍሰሀየ
 የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማህበራዊ ጉዳዮችን፣ መልካም አስተዳደርንና ሪፎርምን፣ ፋይናንስንና ኢኮኖሚን የሚመለከቱ ሶስት የስራ ዘርፎችን ከፍቶ ባለስልጣኖችን የሾመው በስራ ብቃት እንጂ በኢአደግ ውስጥ ለተካተቱት አራት ድርጅቶች እንደ ጠበል መርጫት የስልጣን ድርሻ ለማከፋፈል አይደለም ሲሉ በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሚኒስትር ዲኤታ አቆ ጌቸው ረዳ እንደተናገሩ ይታወሳል።

በኢትዮጵያው የሲቭል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በፌደራል ህገ-መንግስት ዙርያ ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር አሰፋ ፍሰሀ ግን ከመርህ አንጻር ሲታይ በኢሀደግ ውስጥ የተካተቱት አራት ድርጅቶች እኩል ናቸው ተብለው የሚታሰቡ እንደመሆኑ መጠን አራቱንም ድርጅቶች ወደ ከፈተኛው የመንግስት አካል የማምጣት ጉዳይ ይታያል ብለዋል።

ከዚያም አልፎ ኢህአደግ በስልጣን ላይ የሚቆይ ከሆነ የሊቀመንበርነቱ ስልጣን በአራቱ ድርጅቶች መካከል መዘዋወር አለበት ሲሉም ዶክተር አሰፋ
አስገንዝበዋል።
ይህ ፎረም ተዘግቷል
አስተያየቶች
     
እዚህ ፎረም ላይ የሠፈረ አስተያየት የለም፤ ያውጡና የመጀመሪያው ይሁኑ