በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ-ከተማ፣ ህገ-ወጥ የተባሉ ግንባታዎች እየፈረሱ ናቸው



አዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ ክፍለ-ከተማ፣ የረር በር፣ ልዩ ስሙ ጎራ ሰፈራ በወረዳ 9 እና 11 አካባቢ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ መሆናቸው ይሰማል። በዚሁ ክፍለ-ከተማ ደግሞ «ፈረሳው አይመለከታችሁም» የተባሉም አሉ።

ከባለሥልጣናት እንደሚሰማውና ቤታቸው የፈረሰባቸውም ሆኑ በማስጠንቀቂያ ያሉት ‘ተነገረን‘ ብለው እንደሚገልጹት፣ ቤቶቹ በህገ-ወጥ መንገድ የተሰሩ ናቸው። ነዋሪዎች ግን፣ «እስከ ዛሬ ለምን እንደቆዩና አሁን ከምን ተነስተው ህገ-ወጥ ናችሁ እንዳሉን አልገባንም» ይላሉ።

በቦሌ ክፍለ-ከተማ የወረዳ 11 ኃላፊ አቶ ጣሰው ሰቡ ግን ቤቶቹ ህገ-ወጥ ስለሆኑ፣ በተለይም ከገበሬዎች እየተገዙ የተሠሩ በመሆናቸው ነው ብለዋል። ህገ-ወጥ የተባሉት ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ ተጠይቀውም መልስ ሰጥተዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:13:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG