በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ በዋሺንግተን ዲሲ


የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ በዋሺንግተን ዲሲ
የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ በዋሺንግተን ዲሲ

ዴቪድ ሺን - የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣ ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር
ዴቪድ ሺን - የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣ ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:01 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ርዕሰ-ብሔርነቱ በዘለቁ ወቅት ሃገራቸው ከነበረችበት የምጣኔ ኃብት ድቀት አሁን እያገገመች በመሆኗ ትኩረታቸውን ለአፍሪካ እየሰጡ መሆኑን የሚያሳዩ ክንዋኔዎችን እያደረጉ ነው ሲሉ ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር የነበሩትና የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን ገለፁ፡፡

ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት በስተቀር ያልተጋበዙት መሪዎች አለመጋበዝ ትክክለኛ ውሣኔ ነው ብለው እንደማያስቡም ተናግረዋል - አምባሳደር ሺን፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የመጭው ሣምንት የአፍሪካ መሪዎች የዋሺንግተን ጉባዔ ይህንን ጉባዔ የረጥነው ከአፍሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሳደግ መወሰናችንን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የሥልታዊ ግንኙቶች የብሄራዊ ፀጥታ ምክትል አማካሪ ቤን ሮድስ ተናግረዋል፡፡

ሚስተር ሮድስ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ እና የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ፀጥታ ምክር ቤት የልማትና የዴሞክራሲ ከፍተኛ ዳይሬክተር ጌል ስሚዝ ጉባዔውን አስመልክቶ ከትናንት በስተያ ምሽት ላይ ከጋዜጠኞች ጋር ባካሄዱት የአንድ ሰዓት የስልክ ቃለ-ምልልስ የመጭውን ሣምንት ጉባዔ ይዘትና አካሄድ አብራርተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአሜሪካ ባለሥልጣናቱ የሰጡትን መግለጫ ለማንበብ ከላይ የተቀመጠውን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፡፡

http://www.whitehouse.gov/the-press-office/2014/08/01/record-conference-call-us-africa-leaders-summit

XS
SM
MD
LG