ዓርብ, የካቲት 12, 2016 የአካባቢው ጊዜ 08:33

  ድምጽ / ሳምንታዊ ዝግጅቶች

  «ጉዲፈቻ» በአሜሪካ

  “በፊት እንደዚህ፥ ባይሆንስ፥ ባትቀርበኝስ?” የሚል ስጋት ነበረኝ። ያ ሁሉ ግን ልጃችን ከመጣች በኋላ፥ ያ ሁሉ ይረብሸኝ የነበረው ጥያቄ፥ ጠፋ። ወዲያው መጥታ ለወጠችው።” ወ/ሮ ሶፋኒት ተፈራ።

  አሉላ ከበደ
  የመጀመሪያውን የገና በዓል ከአሳዳጊ ወላጆቿ ጋር ባደረገች ህጻን ታሪክ መነሻነት የተቀናበረ ዝግጅት ነው።

  የማጭበርበር ሙከራን ጨምሮ ለሦሥት ዓመታት የዘለቀ ውስብስብና ለመንፈስ ጉዳት ከሚዳርግ ውጣ ውረድ በኋላ ለሦሥተኛ ጊዜ ባደረጉት ጥረት የተገኘ ውጤት ነው፤ ታሪኩ።

  ኢትዮጵያዊ ልጅ በጉዲፈቻ ለማሳደግ በደረሱበት ውሳኔ የተጓዙበትን መንገድ በጨረፍታ የሚያስቃኙን ነዋሪነታቸውን በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ያደረጉት ባልና ሚስት አቶ ሰለሞን ለማና ወ/ሮ ሶፋኒት ተፈራ ናቸው።

  ከአቶ ሰለሞንና ከወ/ሮ ሶፋኒት ጋር ያደረግነውን ቆይታ ከዚህ ያድምጡ፤
  ከአቶ ሰለሞንና ከወ/ሮ ሶፋኒት ጋር ያደረግነውን ቆይታ ከዚህ ያድምጡ፤i
  || 0:00:00
  ...    
   
  X
  ይህ ፎረም ተዘግቷል
  አስተያየቶች
       
  እዚህ ፎረም ላይ የሠፈረ አስተያየት የለም፤ የመጀመሪያው ይሁኑ