በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማንዴላ አረፉ


ኔልሰን ማንዴላ
ኔልሰን ማንዴላ

የነፃነት ትግል ቀንዲል የሆኑት የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ (ማዲባ) አረፉ፡፡


please wait

No media source currently available

0:00 0:09:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ኔልሰን ማንዴላ
ኔልሰን ማንዴላ

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ቀጥተኛ መገናኛ

ሐሙስ፣ ኅዳር 26/2006 ዓ.ም ምሽት ላይ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ይዘው የወጡት መርዶ በቅንጣት በተቆጠሩ ሰከንዶች ውስጥ ዓለምን ያዳረሰ ነበር፡፡ “…ማንዴላ አሁን ሄዱ…”

የነፃነት ትግል ቀንዲል የሆኑት የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ (ማዲባ) አረፉ፡፡

ጃከብ ዙማ - የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት
ጃከብ ዙማ - የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት
ለደቡብ አፍሪካ ባለቀለም ሕዝቦች በዚህች ምድር ላይ መኖር ጥፋት፣ መከራና ድቅድቅ ጨለማ በነበረበት ወቅት ይንጨላጨል የነበረ የተሻለ ሕይወት፤ የተስፋና በዕውኑ ሰው የመሆን ቀንዲል፤…

በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ እጅግ ከከበዱ ጠባሳዎች አንዱ የነበረውን በነጭ ደቡብ አፍሪካዊያን የበላይነት ይመራ የነበረውን የአፓርታይድ ሥርዓት ክፉኛ ጠልተውና ንቀው የሚፋለሙት የነበሩ ወጣት ደቡብ አፍሪካዊያን መገለጫ የሆኑት ኔልሰን ማንዴላ ያኔ ትግሉን ይመራ የነበረውን የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስን የትጥቅ ትግል ክንፍ ይመሩ ነበር፡፡ ስለዚህ ወንጀላቸውም ከዕድሜአቸው ሃያ ሰባቱን በወኅኒ እንዲያሣልፉ ተገድደዋል፡፡

“ሰዎች ሁሉ ተጣጥመውና የዕኩል ዕድሎች ተቋዳሽ ሆነው የሚኖሩበትን የዴሞክራሲያዊና የነፃ ኅብረተሰብን የነጠረ ዓለም ሃሣብ ሳከብር ኖሬአለሁ፤ ይህ ልኖርለትና ልጨብጠውም የምፈልገው ዓለም ነው፡፡ ካስፈለገም ደግሞ ሕይወቴን ልሰጥለት ዝግጁ የሆንኩለት ሃሣብ ነው፡፡”

ኔልሰን ማንዴላ
ኔልሰን ማንዴላ

ማንዴላ ከዚያ በኋላ ለሦስት አሥርት ዓመታት ለዘለቀ ጊዜ ወደኖሩበት ወኅኒ ከመወርወራቸው ቀደም ሲል ነበር ይህንን የተናገሩት፡፡
የጤናቸው ሁኔታ በጣም አሣሣቢ ሆኖ ላለፉት በርካታ ወራት በቅርብ የሕክምና ክትትል ሥር የቆዩት ማንዴላ ኅዳር 26/2006 ዓ.ም በ95 ዓመት ዕድሜአቸው አረፉ፡፡

በቀጥታ በተሠራጨ ንግግራቸው የማዲባን ዜና ዕረፍት ለዓለም ያረዱት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃከብ ዙማ “ለነፃነት ያለመታከት ያደረጉት ትግል የዓለምን ክብር አተረፈላቸው” ብለዋል፡፡

ከል ለብሰው የመርዶ ቃሎቹን ያሰሙት ፕሬዚዳንት ጃከብ ዙማ እንዲህ ብለዋል፡- “የዴሞክራሲያዊት ሃገራችን መሥራች፤ የምንወድዳቸው ኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ አሁን ሄዱ፡፡ በቤተሰቦቻቸው መካከልኅዳር 26/2006 ዓ.ም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ከሃምሣ ደቂቃ ላይ /በኢትዮጵያ - ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከሃምሣ ደቂቃ/ በሰላም አርፈዋል፡፡ አሁን እረፍት ላይ ናቸው፤ አሁን ሰላም ላይ ናቸው፡፡ ሃገራችን እጅግ ታላቅ ልጇን አጣች፤ ሕዝባችንም አባት አጣ፡፡ ምንም እንኳ ይህ ቀን እየቀረበ እንደነበር ቀደም ብለን ብናውቅም፣ እጅግ የጠለቀና የከበደውን የማጣታችንን ስሜት ግን አንዳች ነገር ስንኳ አያቀልለውም… … ኔልሰን ማንዴላ አንድ ላይ ሰብስበውናል፤ የምንሸኛቸውም ሁላችንም አብረን ሆነን ነው፡፡ ለምንወድዳቸው ማዲባ መንግሥታዊ የስንብት ሥነ-ሥርዓት ይደረግላቸዋል፡፡”

ፕሬዚዳንት ጃከብ ዙማ አክለውም ጊዜው ለደቡብ አፍሪካዊያን እጅግ የጠለቀ ኀዘን ጊዜ ደግሞም የደቡብ አፍሪካዊያን የታላቅ ቁርጠኝነት መገለጫ ጊዜም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ማዲባ የደቡብ አፍሪካና የደቡብ አፍሪካዊያን ብቻ የመሆናቸው ታሪክ ከተዘጋ እጅግ የበዙ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ማዲባ የሰው ዘር ሁሉ ናቸው፡፡ …ለእነርሱም መፅናናትን ተመኝተዋል ፕሬዚዳንት ዙማ፡፡ “ማዲባን የራሣቸው አድርገው ያቀፉ፣ እርሣቸው የቆሙላቸውን ቁምነገሮችም የራሣቸው አድርገው የያዙ በመላው ዓለም ያሉ፣ ሚሊዮኖች ሕዝቦችን በኅሊናችን እናስባለን” ብለዋል ዙማ፡፡

የፕሬዚዳንት ጃከብ ዙማን የመርዶ ሙሉ ቃል ከዚህ በታች የተያያዘውን የዌብ ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፤ ቪድዮውን ያገኛሉ፡፡
http://www.youtube.com/watch?v=yO5seNFaxmI

ከኅዳር 27/2006 ዓ.ም አንስቶ የማዲባ የቀብር ሥነ-ሥርዓት እስኪፈፀምም የሃገሪቱ ባንዲራ በየሰንደቁ ላይ በግማሽ ዝቅ ብሎ እንዲሰቀል ማዘዛቸውንም ፕሬዚዳንት ዙማ ተናግረዋል፡፡

የማንዴላን ዕረፍት መነገር ተከትሎ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የራሣቸውንና የሃገራቸውን ኀዘን የገለፁት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ “ኔልሰን ማንዴላ ቀደም ሲል ለተለሙት የነጠረ ሃሣባቸው ኖሩ፣ እውንም አደረጉት” ብለዋል፡፡

“በብርቱው ክብራቸውና በማይጎብጥ ፅናታቸው ማዲባ ደቡብ አፍሪካን ለወጡ፤ ደግሞም ሁላችንንም አነቃነቁን” ብለዋል ፕሬዚዳንት ኦባማ አክለው፡፡

“የታሪክን ሂደት በእጆቹ ጨብጦ የሞራልን ጥልቅ ሁለንተና ደጋን ወደፍትሕ አቅጣጫ ላዞረ ሰው፡፡” - ኦባማ ለማዲባ ክብር ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥታቸው ያስተላለፉትንና በቀጥታ የተሠራጨ መልዕክታቸውን ሲናገሩ - ሐሙስ፤ ኅዳር 26/2006 ዓ.ም
“የታሪክን ሂደት በእጆቹ ጨብጦ የሞራልን ጥልቅ ሁለንተና ደጋን ወደፍትሕ አቅጣጫ ላዞረ ሰው፡፡” - ኦባማ ለማዲባ ክብር ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥታቸው ያስተላለፉትንና በቀጥታ የተሠራጨ መልዕክታቸውን ሲናገሩ - ሐሙስ፤ ኅዳር 26/2006 ዓ.ም

“በኔልሰን ማንደላ ከተነቃቁ ሚሊየኖች አንዱ እኔ ነኝ” ያሉት ኦባማ በዚህም ምክንያት የመጀመሪያው የፖለቲካ አቋማቸውና እንቅስቃሴአቸው አፓርታይድን መቃወም እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡ “… ማንዴላ ከእሥር የተፈቱ ዕለት - አሉ ኦባማ - በፍርሃቱ ሳይሆን በተስፋው ከተመራ የሰው ልጅ ምን ማድረግ እንደሚችል እንድገነዘብ አድርጎኛል” - የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ጥቁር ፕሬዚዳንት ስለመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንት የሚሰማቸውን የጠለቀ ክብር ሲናገሩ፡፡ “እናም - አሉ ኦባማ - በዓለም ዙሪያ እንዳሉት ብዙዎች ሁሉ … የራሴ ሕይወት ኔልሰን ማንዴላ ከደነገጉት ተምሣሌትነት ውጭ ምን ሊመስል እንደሚችል ሙሉ በሙሉ መገመት አልችልም፡፡ በመሆኑም በሕይወት እስካለሁ ከእርሣቸው ለመማር የታደልኩትን እየሠራሁ እኖራለሁ፡፡”
“ያለ ማንዴላ ተምሣሌትነት እኔ ሕይወቴ ምን ልትመስል እንደምትችል መገመት አልችልም” - የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ
“ያለ ማንዴላ ተምሣሌትነት እኔ ሕይወቴ ምን ልትመስል እንደምትችል መገመት አልችልም” - የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ

ደግሞም - አሉ ኦባማ ለማዲባ ክብር ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥታቸው ያስተላለፉትንና በቀጥታ የተሠራጨ መልዕክታቸውን ሲያጠናቅቁ - ኔልሰን ማንዴላ ስለኖሩለት ሕይወት ለአፍታ ቆም ብለን ምሥጋናችንን እንስጥ - ለዚያ - “... የታሪክን ሂደት በእጆቹ ጨብጦ የሞራልን ጥልቅ ሁለንተና ደጋን ወደፍትሕ አቅጣጫ ላዞረ ሰው፡፡”

የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን የኀዘን መግለጫ ለመስማትና ለማየት ከታች ያለውን የዌብ ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፤
http://www.youtube.com/watch?v=eIbwXCbiklY&feature=youtu.be

ሚስተር ኦባማ ኀዘናቸውን በሃገራቸውና በመንግሥታቸው፣ በባለቤታቸው ሚሼል ኦባማና በቤተሰባቸው እንዲሁም በራሣቸው ስም ከገለፁ በኋላ እና ከዚያም በፊት የቀድሞዎቹ ፕሬዚዳንቶች ጆርጅ ቡሽ - ቀዳማዊ፣ ጆርጅ ቡሽ - ዳግማዊ፣ ቢል ክሊንተን ከባለቤቶቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው ያስተላለፏቸው የኀዘን መልዕክቶች በየመገናኛ ብዙኃኑ ተደምጠዋል፡፡

ዓለም ከየአቅጣጫው ኀዘኑን እያሰማ ነው፡፡ በዓለም ዙሪያ የኀዘን ቀን፣ የኀዘን ጊዜ ነው፤ መላ የሰው ልጅ አንድ ውድ ሃብቱን በሕይወት አጥቷልና፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ እንዲህ አሉ - “እንግዲህ እርሣቸው የእኛ አይደሉም፤ እርሣቸው የዘለዓለማዊነት ናቸው፡፡”

XS
SM
MD
LG