በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ሥርጭት ወደ 1.3 ከመቶ ወረደ


በኤድስ ላለፉ ሁሉ መታሰቢያ
በኤድስ ላለፉ ሁሉ መታሰቢያ

በዓለም ዙሪያ 35 ሚሊየን ሰው ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ እንደሚገኝ ተገለፀ፤ “አሜሪካ ፍልሚያውን በመምራት ትቀጥላለች”


ዜሮ ኤድስ
ዜሮ ኤድስ


please wait

No media source currently available

0:00 0:21:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዓለም ዙሪያ 35 ሚሊየን ሰው ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ እንደሚገኝ ተገለፀ፤ “አሜሪካ ፍልሚያውን በመምራት ትቀጥላለች”
ትናንት ታስቦ የዋለውን የዓለም የኤድስ ቀን አስታክኮ የተባበሩት መንግሥታት ፀረ-ኤድስ መርሃግብር ባወጣው ሪፖርት ባለፉት ሰላሣ ዓመታት በኤድስ ምክንያት ከሃያ አምስት ሚሊየን በላይ ሰው በመላው ዓለም ሕይወቱ ማለፉን ገልጿል፡፡

አፍሪካና ኤድስ
አፍሪካና ኤድስ
በሌላ በኩል ግን ኤድስን በመዋጋት የተሣካ ሥራ አከናውነዋል ከሚባሉት ሃገሮች አንዷ በሆነችውና በወረርሽኙ ክፉኛ በተጎዳችው ኢትዮጵያ የሥርጭቱ መጠን ከአሥርና አሥራ አምስት ዓመታት በፊት እንደነበረ ከሚነገረው ሰባት ከመቶ ዛሬ ወደ 1.3 ከመቶ መውረዱ ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያ የእናቶችንና የሕፃናትን ሞት በመቀነስ በኩል ሰፊ ሥራ እያከናወነች መሆኑን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊው አቶ ተገኔ ረጋሣ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ለዝርዝሩ ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Obama World AIDS Day
Obama World AIDS Day
በሌላ በኩል ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኅዳር 22ን የዓለም የኤድስ ቀን ሆኖ በመላ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ታስቦ እንዲውል ሰሞኑን በፊርማቸው ባወጡት አዋጅ ጦርነቱ ዓለምአቀፍ ጦርነት መሆኑን አመልክተው በጦርነቱ ውስጥ አሜሪካ በመሪነቷ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

(የፕሬዚዳንታዊውን አዋጅ ሙሉ ቃል ለማንበብ ከታች ያለውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ)http://www.whitehouse.gov/the-press-office/2013/11/27/world-aids-day-2013
XS
SM
MD
LG