በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጉዲፈቻ ልጅ ፍለጋ የተደረገ የአንድ ቤተሰብ የሦሥት ዓመት ጉዞ


“በሂደቱ፥ መጀመሪያ ካገኘናቸው ልጆች ጋር ቅርርብ ፈጥረን ስለነበር፥ ሁኔታው ሲሰናከል በእጅጉ ብናዝንም፤ የተለየ አቀራረብ መከተል መረጥን እንጂ፤ ተስፋ አልቆረጥንም።” አቶ ሰለሞን ለማ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:10:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:12:21 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:12:13 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከሦሥት ዓመታት እጅግ አድካሚ ጥረትና ከሦሥት ሙከራዎች በኋላ በመጨረሻው ለአሳዳጊ ወላጅነት የበቁ፥ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ባልና ሚስት ናቸው።

በአገሪቱ የተደነገጉትን የጉዲፈቻ አፈጻጸም የሚመራባቸውን ኅጎች ተከትለው በደምቡ መሠረት የሚያሳድጉት ልጅ ፍለጋ ወደ አገራቸው የተጓዙት ባልና ሚስት፥ ኅግን ማክበርና መከተል ብቻውን ህልማቸውን እውን ለማድረግ ቀላል አላደረገላቸውም።

ለተደጋጋሚ አሳዛኝ አጋጣሚዎችና የመጭበርበር ሙከራዎችም ጭምር ቢያጋለጡም፤ ተሥፋ ሳይቆርጡ ውጣ ውረድ ከበዛው ረጅም ጉዞና ያልታከተ ጥረት በኋላ በመጨረሻው የአንዲት በጊዜው ዓመት ያልሞላት ህጻን አሳዳጊ ወላጆች የሆኑበትን አጋጣሚና ፈተናዎች፤ “ተሞክሯችን በእኛ መንገድ ለሚሄዱ ሌሎች ትምህርት ቢሆን፤” ሲሉ አካፍለውናል።

አቶ ሰለሞን ለማና ወ/ሮ ሶፋኒት ተፈራ ይባላሉ። ከልጃቸው የመጀመሪያ ገና ገጠመኞች ጋር ለገና ዋዜማ አብረውን ያመሹት አቶ ሰለሞንና ወ/ሮ ሶፋኒት ባለ ሦሥት ክፍል ወጎች ያድምጡ።
XS
SM
MD
LG