በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ዚምባብዌ አዲስ ዓለምአቀፍ ብድር ልታገኝ የምትችለው፣ በርካታ ለውጦችን ተግባራዊ ካደረገች ነው"- ሴናተር ባብ ኮርከር


ፋይል ፎቶ - የዚምባብዌ ገበሬ እአአ 2016
ፋይል ፎቶ - የዚምባብዌ ገበሬ እአአ 2016

"ዚምባብዌ አዲስ ዓለማአቀፍ ብድር ልታገኝ የምትችለው፣ በርካታ ለውጦችን ተግባራዊ ካደረገች ነው" በማለት የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር ባብ ኮርከር የሰጡትን አስተያየት፣ የዚምባባዌው የገንዘብ ሚኒስትር ፓትሪክ ቺናማሳ ውድቅ አደረጉት።

"ዚምባብዌ አዲስ ዓለማአቀፍ ብድር ልታገኝ የምትችለው፣ በርካታ ለውጦችን ተግባራዊ ካደረገች ነው" በማለት ዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር የውጪ ግንኙነት ኰሚቴ ሊቀ-መንበር ከሴናተር ባብ ኮርከር የሰጡትን አስተያየት፣ የዚምባባዌው የገንዘብ ሚኒስትር ፓትሪክ ቺናማሳ ውድቅ አደረጉት።

ሴናተር ባብ ኮርከር ባለፈው ሳምንት ነበር ይህን ሃሳብ ያቀረቡት። ጥያቄው የተሰነዘረው፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትን ተወክለው እንደ የዓለም ባንክ፣ ዓለማቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የአፍሪቃ ልማት ባንክ ውስጥ ለሚገኙ ባለሥልጣናት ሲሆን፣ ጥያቄውም፣ "ዚምባብዌ የሰብዓዊ መብት ይዞታዋንና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አካሄዷን ካላሻሻለች፣ ምንም ዓይነት የብድር ጥያቄ እንዳስይሰተናገድ" የሚል ነበር።

ይህን ለዩናይትድ ስቴትሱ የገንዘብ ሚኒስትር ጃክ ልው የተላከውን ደብዳቤ በተመለከተ፣ የዚምባብዌው የገንዘብ ሚኒስትር ቺናማሳ ሲመልሱ፣ "ዚምባብዌ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሴናተር ኮርከር የሚያውቁት ነገር የለም" ብለዋል። "ዚምባብዌን በተመለከተ በብዙ ነጥቦች ዙሪያ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል። ስለ ዚምባብዌ የተዛቡ መረጃዎችን ይዘው ብቻ መንጎድ የለባቸውም። በመደመሪያ ደረጃ ሴናተሩ፣ ከእኛ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የዓለም ባንክ፣ የአፍሪቃ ልማት ባንክንና፣ ዓለማቀፍ የገንዘብ ድርጅትን (IMF)በጉዳዩ ላይ ማሳተፍ ነበረባቸው። ሴናተር ባብ ኮርከር ይህን አቋም መያዛቸው ግን አስደንቆናል።" በማለት አክለዋል።

የዚምባብዌው የገንዘብ ሚኒስትር በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ገደማ በተናገሩት ቃል፣ አዲስ የተሰየሙት አምባሳደር ሄሪ ቶማስ ጁንየር በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡበት እንዲያደርጉና፣ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማም ስለ ፕሬዚደንት ሮቤርት ሙጋቤ መንግሥት ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማድረግ ማቀዳቸውን ገልጸዋል።

የዚምባብዌው ፕሬዚደንት በአገሪቱ የህግ የበላይነትን እንዲያከብሩና ትክክለኛና አሳማኝ የምርጫ ሁኔታዎችን እንዲያስቀምጡ የሚጠይቅ ደብዳቤ ነው፣ ሴናተር ኮርከር የጻፉት። እነዚህ ሁኔታዎች ካልተሟሉ፣ በአበዳሪ ተቋማቱ ውስጥ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ልዑካን፣ ከዚምባብዌ ለሚመጣ የብድር ጥያቄ፣ አሉታዊ መልስ እንዲሰጡ ነው፣ ሴናተሩ በደብዳቤያቸው ያሳሰቡት በሴናተር ኮርከር ደብዳቤ መሠረት፣ ዚምባባዌ ለዓለም ባንክ፣ ለዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና ለአፍሪቃ ልማት ባንክ፣ የ$1.9 ቢልዮን ባለ ዕዳ ነች። ከአራሬ የደረሰን የሰባስትያን ሞፉ ዘገባ አለ፤ አዲሱ አበበ አቅርቦታል። ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG