በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዚምባብዌ ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት የስም ማጥፋት ወንጀል ህግ ሰረዘ


የዚምባብዌ ጋዜጠኞች በህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት
የዚምባብዌ ጋዜጠኞች በህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት

የዚምባብዌ ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት የስም ማጥፋት ወንጀል ህግን ሰርዟል። የተሰረዘው ህግ ባለፈው አመት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች እንዲታሰሩ ምክንያት ሆኗል።

የዚምባብዌ ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት ዳኞች የስም ማጥፋት ህጉን በሙሉ ድምጽ የሰረዙት ቨንድራዳ ሙንዮሮ (Vendrandah Munyoro) የተባሉ የጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ባለስልጣን እንዲህ አይነቱ ህግ በዲሞክራሲ ቦታ እንደሌለው አምነው ከተቀበሉ በኋላ ነው።

ፍርዱ ከተሰጠ በኋላ ባለስልጣንዋ ጋዜጣኞችን ማነጋገር አልፈለጉም።“መናገር አይፈቀድልኝም። (ፍርድ ቤት ውስጥ ሲናገሩ አልነበረም እንዴ) እሱ ፍርድ ቤት ውስጥ ነው። (ምንድነው ልዩነቱ?) አሁን ከፍርድ ቤቱ ውጭ ነጭ ያለሁት።” ብለዋል።

የደቡባዊ አፍሪቃ የሚድያ ተቋም ጋዜጠኞች ባቀረቡት ማመልከቻ የስም ማጥፋት ወንጀል የሚለው ህግ ህገ-መንግስታዊ መሰረት የለውም። በአዲሱ የዚምባብዌ ህግ የተሰጠውን የሚድያ ነጻነት ይጥሳል ሲሉ ተከራክረዋል።

የደቡበዊ አፍሪቃ የሚድያ ተቋም የዚምባብዌ ቅርንጫፍ ሃላፊ ነህላንሃል ንግወንያ (Nhlanhla Ngwenya) በውሳኔው ለመፈንጠዝ ገና ነው ብለዋል።

“ይህ ትንሽ ድል ነው። ምክንያቱም የጋዜጠኝነት ሙያን ወንጀል ሊያደርጉ የሚችሉ ገና ብዙ ህጎች አሉና። ዚምባብዌ ገና ልትታገላቸው የሚገባ ብዙ ህጎች አሉ። ይህ ሲባል ግን የስም ማጥፋት ወንጀል የሚለው ህግ የገዢው አካል አባላት ልሂቃን ጋዜጠኞችን ለማጥቃት የሚያዘወትሩት መሳርያ ነው የነበረው።”ይላሉ ነህላንሃል ንግወንያ።

ጋዜጠኞች እንዲሰረዝ የሚፈልጉት ሌላ ህግ ካቢኔ ስላደረገው ስብሰባ ከ 25 አመታት ባነሱ ጊዜያት ውስጥ መዘገብ ወንጀል የሚያደርገው የኦፊሴላዊ ሚስጢር ህግ የተባለው ነው። ከአራት አመታት በፊት ስለታተመ ዘገባ የስም ማጥፋት ህጉን በሚመለከት የፕረዚዳንት ሮበርት ሙጋቤን መንግስት ከከሰሱት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነካባ ማትሻዚ (Nkaba Matshazi) የተባለው የንውስ ዴይ (The News Day) የግል ጋዜጣ አዘጋጅ ነው። አሁንም ቢሆን በጋዜጠኞች ላይ የስም ማጥፋት ክስ ሊቀርብ ስለሚችል ጋዜጠኞች መጠንቀቅ እንዳለባቸው አውስቷል።

“አሁንም ቢሆን ሃላፊነት በጎደለው መንገድ ለመጻፍ ይቻላል ማለት አይደም። የጋዜጠኝነትን ስነ-ምግባር፣ እውነትንና ርቱዕነትን መከታል ያስፈልጋል። ርትእን መከተል ይኖርብናል። አለበለዚያ ልንከሰስ እንችላለን።”ብለዋል።

ዚምባብዌ የሚድያ ነጻነት ከጠበበባቸው የአፍሪቃ ሀገሮች አንዷ ናት። እአአ ከ 2000 ዎቹ የመጀመርያ አመታት አንስቶ በርካታ ጋዜጠኞች ታስረዋል። አንዳንዶቹ ደገሞ በተለያዩ የሚድይ ህጎች መሰረት አጥፍተዋል ተብለው ከሀገር እንዲወጡ ተደርጓል።

የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ሰባስትያን ሞህፉ (Sebastian Mhofu) ከሀራሬ ዘገባ ልኳል። አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች። ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

የዚምባብዌ ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት የስም ማጥፋት ወንጀል ህግ ሰረዘ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:41 0:00

XS
SM
MD
LG