በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከስደት ኑሮ ወደ ከፍተኛ የትምህርት እድል


ናዝራዊ ኢያሱ(ግራ) እና ወንድሙ ሻሎም ኢያሱ(ቀኝ)
ናዝራዊ ኢያሱ(ግራ) እና ወንድሙ ሻሎም ኢያሱ(ቀኝ)

ናዝራዊ ኢያሱ አባቱ ኢትዮጵያዊ እናቱ ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው። ወላጆቹ እኤአ ከ2001 ዓ. ም. ጀመሮ በኬንያ በስደት ነው የኖሩት። ኬንያ እንደመጡ ከናይሮቢ 180 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘዉ ናሮክ ከተማ ኑሯቸውን መሰረቱ።

ከቤተሰቡ 11 ልጆች ናዝራዊ የመጀመሪያው ነው።

በ2013 ቤተሰቦቹ ወደ ካኩማ የስደተኞች ጣቢያ ሲዛወሩ፤ እሱም ከእነሱ ጋር ወደ ካኩማ በማምራት በስደተኞች ካምፕ ሌላ የስደት ኑሮን ቀጥሏል።

በየካናዳ ዓለም አቀፍ የትምህርት አገልግሎት ለስደተኞች የሚሰጠዉን የትምህርት ዕድል በ2015 ተወዳድሮ አሸንፎአል።

በካኩማ የስደተኞች ካምፕ ነዋሪው ናዝራዊ በቅርቡ በካናዳ ትምህርቱን ለመከታተል ወደ ቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ ያመራል።

ቤተሰቦቹ በችግር በስደት እንዳሳደጉት የሚገልጸው ናዝናዊ ደስታውን ገልጾ “ ከአቅማቸዉ አንጻር ልጆች ማሳደግ የነበራቸዉም ብዙም ደግሞ ገቢ የሚሰጥ ሥራ አልነበራቸዉም ስለዚህ ችግር ነበረ እኔን ለመደገፍ ትምህርት ቤት፣ ማለት መጀመርያ ከ1 ክፍል እስከ 8 ኛ ክፍል ያዉ ለዩኒፎርም፣ ለደብተር፣ ለጫማ አባቴ ሁሌ ከቢሮ ወደ ቢሮ እየዞረ ነበር አጋዥ ማፈላለግ”

“እናቴ ማንዳዚ ትሰራለች ማንዳዚ ማለት ኬንያ ዉስጥ የሚሰራ ዳቦ ነገር ነዉ፣ እሱን ታበስል እና ትሸጣለች፣ አባቴ ደግሞ ያገኘዉን ሥራ ይሰራ ነበር።”

ናዝራዊ አሁን ለቀጣይ ትምህርቱ የሚጠቅሙ ስልጠናዎችን እዚያው ካኩማ በመዉሰድ ላይ ይገኛል። ዊንድልትራስት ኬንያ የተባለዉ የበጎ አድራጎት ድርጅት እሱንና ሌሎች 22 ወጣት ስደተኞችን እያሰለጠነ ሲሆን በሚቀጥለዉ ነሃሴ ናዝራዊና 22ቱ ጓደኞቹ ትምህርታቸዉን ለመቀጠል ወደ ካናዳ ያመራሉ።

ከፍተኛ ትምህርቱን በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ ለመቀጠል በመጪው ነሃሴ ወደ ካናዳ የሚሄደው ናዝራዊ ትምህርቱን ሲያጠናቅቅ ወደ ትዉልድ ሃገሩ ተመልሶ መሥራትን ያስባል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ከስደት ኑሮ ወደ ከፍተኛ የትምህርት እድል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG