በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በየመንዋ አደን ከተማ ውስጥ ዛሬ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ


ፋይል ፎቶ - ሰንአ የመን ውስጥ
ፋይል ፎቶ - ሰንአ የመን ውስጥ

አጥቂው ቦምቡን ያፈነዳው የየመኑ መንግስት በሳውዲ አረቢያ በሚመራው ህብረት ሃይሎች ርዳታ ሁቲዎቹን ተዋጊዎች አባርሮ መቀመጫው ባደረጋት ከተማ በተሰባሰቡ ምልምል ወታደሮች መሃል መሆኑ ታውቋል።

የየመንዋ ደቡባዊ የወደብ ከተማ አደን ውስጥ ዛሬ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ። ይህ የሆነው በመንግስት ወገንተኞቹ ሐይሎችና በሁቲዎቹ አማጽያን መካከል የተጀመረው የተኩስ አቁም ውል ሁለተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬ ዕለት ሲሆን አልፎ አልፎ ተኩስ እንዳለም ይሰማል።

አጥቂው ቦምቡን ያፈነዳው የየመኑ መንግስት በሳውዲ አረቢያ በሚመራው ህብረት ሃይሎች ርዳታ ሁቲዎቹን ተዋጊዎች አባርሮ መቀመጫው ባደረጋት ከተማ በተሰባሰቡ ምልምል ወታደሮች መሃል መሆኑ ታውቋል።

በሚቀጥለው ሳምንት በመንግስቱና በሁቲዎቹ መካከል የሰላም ድርድር ያዘጋጀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድርድሩ በጥሩ ድባብ እንዲጀመር ሁሉም ወገኖች በተኩስ አቁሙ እንዲገፉ እየተማጸነ ነው።

ተኩስ አቁሙ ከታወጀ በኋላ አልፎ አልፎ ሁከት እንደነበር ትናንት ያስታወቀው የመንግሥታቱ ድርጅት አብዛኛው ግጭት በደቡቡዋ ታኢዝ ከተማ እንደነበር ገልጹዋል።

ተኩስ አቁሙ መታወጁን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ከታናንት ሰኞ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄድ የልጅነት ልምሻ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ጀምሯል። በክትባቱ አምስት ሚሊዮን ህጻናትን ለማዳረስ አቅዷል።

XS
SM
MD
LG