በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓናማ ዶክሜንቶች በዓለም ባንክ ጉባዔ ፊት


በዓለም ባንክ የአስተዳደር ኃላፊ ሁለተኛው ከፍተኛ ባለሥልጣን ሲሪ ሙልያኒ ኢንድትራዋቲ
በዓለም ባንክ የአስተዳደር ኃላፊ ሁለተኛው ከፍተኛ ባለሥልጣን ሲሪ ሙልያኒ ኢንድትራዋቲ

የፓናማ ዶክሜንቶች (Panama Papers) በመባል የሚታወቀው፣ የበርካታ የዓለም መሪዎችና ባለጠጎች ምስጢር ያለበት ዶክሜንት የሕዝብን አመኔታ ያሳጣል፣ ዜጎችም ለአገራቸው ትምህርት ቤቶች፣ መንገዶችና ለሌሎች ተቋማት ግንባታ የሚያደርጉትን አስተዋፅዖም ይገድባል፣ ቀረጥ ከመክፈልም ይቆጠባሉ ሲሉ፣ የዓለም ባንክ ሁለተኛው ከፍተኛ ባለሥልጣን አስታወቁ።

ባለሥልጣኗ ሲሪ ሙልያኒ ኢንድትራዋቲ(Sri Mulyani Indtrawati) ከቪኦኤው ጂም ራንድል (jim Randle) ጋር ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ህግ አውጪዎች አዳዲስ ደንቦችን እንዲቀርጹና የበለጠም እንዲቀራረቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ፓናማ ውስጥ ከሚገኙ የህግ ቢሮዎች ሾልከው የሚወጡ ወረቀቶች (ሰነዶች)፣ በመላው ዓለም የሚገኙ አንዳንድ ሀብታሞች ንብረት እንዲያሸሹ፣ ቀረጥም እንዳይከፍሉ ምክንያት ሆነዋል።

የዓለም መሪዎችን ሃብትና ሙስና የሚያጋልጥ ሰነድ ፓናማ ከሚገኝ ኩባኒያ ሾልኮ ወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:41 0:00

ይህ ዓይነቱ አካሄድ ህገ-ወጥ ነው ባይባል፣ በዩናይትድ ስቴትስና በሌሎች አገሮችም የሚገኙ ህግ-አውጪዎች፣ ህጋዊ መሆኑን ይደግፋሉ። እናም ብዙዎቹ፣ ንብረት ማሸሽ ህገ-ወጥ እንደሆነ የሚያስረዳ፣ አዲስና ጠበቅ ያለ ህግ እንዲወጣ ይሻሉ።

ልሂቃኑ ቀረጥ መክፈልን ሲያቆሙ፣ ተራው ሕዝብ ደግሞ አድልዎ እንደተደረገበት በመቁጠር ቅሬታ ያሰማል። በዓለም ባንክ የአስተዳደር ኃላፊ የሆኑት ባለሥልጣን እንደሚሉት፣ አስተሳሰቡ በራሱ አመኔታን ያጠፋል፤ የኤክኖሚ ዕድገትን ይጎዳል። "እነዚህ አገሮች አንዳንድ መሪዎች፣ ልሂቃን ወይም ከዚህ አኳያ ሀብታሞቹ በውጪ አገር የባንክ ሂሳብ እንዳላቸው ሲይቁ፤ 'ለምን?' የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። ይሄ በእውነት ተገቢ ወይም ህጋዊ ሚክናት ነው? የሚል ቅሬታም ያቀርባሉ።"

አገሮች በጋራ ተባብረው ሊሰሩ ይገባል። ዓለማቀፍ ትብብር ከሌለ፣ እነዚህን ከቀረጥ ክፍያ የሚሸሹትን ማሳደድና ማግኘት አይቻልም።
የዓለም ባንክ የአስተዳደር ድሬክተር ሲሪ ሙልያኒ ኢንድትራዋቲ

ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ (Global Financial Integrity) በመባል በሚታወቀው የምርምርና የመብት ተሟጋች ድርጅት ውስጥ የሚገኙ ጠበብት፣ ቶም ካርዳሞን ደግሞ እንዲህ ይላሉ፣ የመንግሥትን ካዝና በእጅጉ መራቆት ያወሳሉ። "ያሉን መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በያአመቱ በትሪልዮን ወይም በአንድ ሺህ ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከታዳጊ አገሮች ይወጣል። ይሄ ደግሞ ወደነዚህ አገሮች ከሚገባው ከውጪ አገሮች ሙኣለ-ንዋይና የውጪ ዕርዳታዎች የሚበልጥ ነው።" ብለዋል።

ከፓናማ ሰነዶች ጋር የተያያዙ ታሪኮችን በሚያወጣ አንድ ዓለማቀፍ ቡድን ውስጥ የሚሠራ የምርመራ ጋዜተኛ እንዳመለከተው፣ ዶክሜንቶቹ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኩባንያዎችን ይፋ ያደርጋሉ። እናም ህጎቹን በተመለከተ ሲናገር፣ "ብዙ ጠበብት እንደሚነግሩን፣ በየ አገሮቹ ያሉ ህጎች መቀየር ይኖርባቸዋል።" ብሏል።

የቀድሞ የኢንዶኔዥያ የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩትና አሁን የዓለም ባንክ የአስተዳደር ድሬክተር ሲሪ ሙልያኒ ኢንድትራዋቲ "አገሮች በጋራ ተባብረው ሊሰሩ ይገባል" ይላሉ። "ዓለማቀፍ ትብብር ከሌለ፣ እነዚህን ከቀረጥ ክፍያ የሚሸሹትን ማሳደድና ማግኘት አይቻልም።" ብለዋል።

እናም፣ የባንክ ሙያተኞች፣ ህጎቹን ለማጥበቅ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ፣ በዋሽንግተን ዲሲው የዓለም ባንክና የዓለማቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF)ስብሰባ ላይ ብርቱ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል።

የፓናማ ዶክሜንቶች በዓለም ባንክ ጉባዔ ፊት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG