በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአለም የጤና ድርጅት የዚካ ቫይረስ መዛመትን ለመግታት 56 ሚልዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገለጸ


ማይክሮሰፋሊ (Microcephaly)ያጠቃው የአራት ወር ህጻን ብራዚል ውስጥ እ.አ.አ 2016
ማይክሮሰፋሊ (Microcephaly)ያጠቃው የአራት ወር ህጻን ብራዚል ውስጥ እ.አ.አ 2016

በሽታው በሚወለዱ ህጽናት ላይ የአካል ጉዳት እንደሚያደርስ ታውቋል።

የአለም የጤና ድርጅት የዚካ ቫይረስን መዛመት ለመግታት ያወጣውን ስትራቴጂ ለመተግበር $56 ሚልዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገልጿል።

በሽታው በሚወለዱ ህጽናት ላይ የአካል ጉዳት እንደሚያደርስ ታውቋል።

የአለም የጤና ድርጅት ስትራቴጂ ሀገሮች የዚካ ቫይረስንና ታያያዥ በሽታዎን የመከታተል ስራ እንዲያዳብሩ ለመርዳት አጋሮችን፣ ጠበብትንና የገንዘብ ምንጭን ማስተባበር እንደሆነ ዛሬ ገልጿል።

የአለም የጤና ድርጅት የሚያስፈልገውን ያህል ገንዘብ እስከሚያገኝበት ጊዜ ድረስ በሽታውን ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ ገንዘብ እንደመደበ ጠቁሟል። ገንዘቡ በጤናው ድርጅትና ዚካ ቫይረን በመታገል ተግባር በተሰማሩ አለም አቀፍ አጋሮች መካከል እንደሚከፋፈል አስታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ድርጅት በዚካ ያወጣው አዲስ ማስጠንቀቅያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:18 0:00

XS
SM
MD
LG