በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢቦላ ቫይረስ በምዕራብ አፍሪቃ ዛሬ በሚያበቃው ዓመት ተሸንፏል


የኢቦላ ቫይረስ በምዕራብ አፍሪቃ ዛሬ በሚያበቃው ዓመት ተሸንፏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:05 0:00

የኢቦላ ቫይረስ በምዕራብ አፍሪቃ ዛሬ በሚያበቃው ዓመት ተሸንፏል

ኢቦላ ቫይረስ ዛሬ በሚያበቃው 2015 ዓመት ሶስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል። ሆኖም ቫይረሱ በምዕራብ አፍሪቃ ተሸንፏል።

ምዕራብ አፍሪቃ ዛሬ በሚያበቃው ዓመት ብዙ ውጣ ውረድ አይቷል። ላይቤርያ ከኢቦላ ነጻ ሆናለች በታባለበት ጊዜ ደስታ በሽታው ተመሶ ለተጫምሪ ሞቶች ምክንያት ሲሆን ደግሞ የመሸነፍ ስሜት ሰፍኖ ነበር። ደግነቱ ግን ቫይረሱን እንደገና በፍጥነት ለመገደብ ተችሏል። ሲየራልዮን ባለፈው ወር ከኢቦላ ነጻ እንደሆነች ተገልጿል።

ጊኒም ለሁለት አመታት ያህል ኢቦላ ቫይረስን ስትታገል ከቆየች በኋላ ከበሽታው ነጻ መሆንዋ ተገልጿል። የአለም የጤና ድርጅት ልዩ የኢቦላ ጉዳይ ተወካይ ዶክተር ብሩስ አይዋርድ (Bruce Aylward) ጊኒ ከኢቦላ በሽታ ነጻ መሆንዋን ያስታወቁት የያዝነው አመት ከማብቃቱ በፊት ነው። "በሶስት አመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ በሶስቱ ሀገሮች የበሽታው መተላለፍ ሰንሰለቶች አቁመዋል ለማለት እንችላለን”ብለዋል።

ኢቦላ በሽታ መዛመት የጀመረው እአአ በታህሳ ወር 2013 አም አንድ ህጻን ልጅ በጊኒ ደን አከባቢ በሽታው ከያዘው በኋላ እደሆነ የአለም የጤና ድርጅት ገልጿል። ከ 28,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኢቦላ በሽታ ተይዘው 11,000 አልቀዋል።

በሽታው ሊመለስ እንደሚችል ዶክተር አንተኒ ፋውቺን (Anthony Fauci) የመሳሰሉት በዩናትድ ስቴትስ (United States) ብሄራዊ የጤና ተቋም የሚሰሩ ጠበበት ያሳስባሉ።

"በጤና ጥበቃ ዘርፍ የምንሰራው ሰዎች ሁሉ ኢቦላ እንደገና ተመልሶ ይዛመታል የሚል እምነት አለን። መዘጋጀት ያለብንም ለዚህ ነው”ይላሉ በበኪላቸው።

የዩናትድ ስቴትስ (United States) የበሽታ መቆጣጠርያ ማዕከል ሃላፊ ዶክተር ቶም ፍሪደን (Tom Frieden) ባለፈው አመት ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ሲናገሩ ዋናው አላማ ጊኒ፣ ላይቤርያና ሲየራልዮን ጣንካራ የጤና ጥበቃ ስርአት እንዲኖራቸው ማድረግ ነው።

“ከዚህ ሁሉ የምንጠብቀው ነገር የኢቦላ በሽታን መዛመት ማቆም ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ኢቦላ እንዳይከሰት ለማቆም የሚያስችል ቤተ-ሙከራ፣ የሰው ሃይልና የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ብቃት እንዲኖር ማድረግ ነው”ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ ኢቦላን ሊያቆም የሚችል ክትባት ስላለ ሌላ አስከፊ የኢቦላ መዛመት ላይኖር እንደሚችል ጠበበት ይናጋራሉ። በያዝነው አመት ቀደም ሲል በጤና ጣብያዎች በተሞከረው መሰረት ክትባቱ እንደሚሰራ ተገልጿል።

የአለም የጤና ድርጅት አላማ በሶስቱ ሀገሮች በተለይም የናቶችና የየልጆች ጤና አጠባበቅን የመሳሰሉት ዋና ዋና የጤና አጠባበቅ መርሀ-ግብሮችን ማጠናከር እንደሆነ ድርጅት አስገንዝቧል።

የአለም ባንክ በበኩሉ ኢቦላ ቢከሰት በእንጭጩ ለመቅጨት እንዲቻልና ለኢኮኖሚ ማገገም የሚያስፈልግ ከ $1.5 ቢልዮን ዶላር በላይ እንዳስተባበረ አስታውቋል።

የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ካሮል ፒርሰን (Carol Pearson) ባጠናቀረችው ዘገባ። አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የኢቦላ ቫይረስ በምዕራብ አፍሪቃ ዛሬ በሚያበቃው ዓመት ተሸንፏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:12 0:00

XS
SM
MD
LG