በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጎንደር የዛሬ ውሎ


ጎንደር ከተማ
ጎንደር ከተማ

የወልቃይት የአማራ ሕዝብ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን ሰዎች ከያሉበት እየታሠሩ እንደሆነ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎ ይናገራሉ። በሰሞኑ ጉዳይ ላይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል። ጽዮን ግርማ ነች ያነጋገረቻቸው።(ሙሉው ቃለ ምልልስ ነገ (ቅዳሜ) ምሽት ይቀርባል)።

በጎንደር ከተማ ከሐምሌ አራት ጀምሮ በመንግሥት ኃይሎችና በሕዝቡም መካከል በተፈጠር ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱ፣ ንብረት መቃጠሉን ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል። ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት ጎንደር ከተማና በአጠቃላይ በአማራ ክልል እንየሰሞኑን በአደባባይ ሰዎች በብዛት ባይታዩም ውስጥ ውስጡን ግን ሰዎች መንቀሳቀስ እንዳቃታቸውና እየታሠሩ መሆኑን አቶ ዋሲሁን አንበሴ ይናገራሉ።

አዲስ አበባ የሚገኙና የወልቃይት ተወላጅ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ሃይሉ አንበሴ በበኩላቸው አዲስ አበባ ያሉ የወልቃይት ተወላጆች ዛሬ መታሰራቸውን ይናገራሉ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የተፈጠረውን ሁኔታ ለማብረድ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ነገር ተረጋግቶ ነገሮች ወደነበሩበት እየተመለሱ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘገባው የጽዮን ግርማ ነው ቀጥሎ ይቀርባል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

የጎንደር የዛሬ ውሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ጽዮን ግርማ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጋር ያደረገችው ቃለ ምልልስ ነገ (ቅዳሜ) ምሽት ይቀርባል።

XS
SM
MD
LG