በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወልቃይት ህዝብ ማንነት ዙሪያ የተጠናቀረ ዝግጅት


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በሰሜን ኢትዮጵያ ሁመራ ምእራባዊ ዞን ወልቃይት የሚኖሩ ወገኖች፣ 20 አባላት ያሉት ”የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ”የተባለ ኮሚቴ መስረተዉ ስለ ማንነታቸው ግንዛቤ እያስጨበጡ መሆናቸውን ይናገራሉ።

በሰሜን ኢትዮጵያ ሁመራ ምእራባዊ ዞን ወልቃይት የሚኖሩ ወገኖች ”የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ” የሚል 20 አባላት ያሉት ኮሚቴ መስረተዉ፣ አማራ እንጂ የትግራይ ተወላጆች አይደለንም፣ ሕወሃት በኢትዮጵያ ስልጣን ሲቆጣጠር በጦር ድል መቶ አካባቢዉን ጠቀለለ ይላሉ።

በዚህ ዙሪያ ጥያቄ ለማሰማትና ግንዛቤ ለማስጨበጥ በልዩ ልዩ እርከን ላይ ያሉ ከፍተኛና የአካባቢ መንግስት ባለስልጣናትን አነጋግረናል ይላሉ። ጥያቄያቸዉ በህገ መንግስቱ መሰረት ህዝበ ዉሳኔ ተካሄዶ የነዋሪዉ ማንነት ይወሰን የሚል ነዉ።

የሁመራ ምእራባዊ ዞን የወልቃይት ባለስልጣናት ግን ኮሚቴዉ የሕዝብ ዉክልና የሌለዉ ሕገ-ወጥ ነዉ። ወልቃይት የትግራይ እንጂ የአማራ ክልል አይደለም ይላሉ።

"የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ” ኮሚቴ አባላት ስለ ጥያቄያቸዉ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ወደ የመንግስት አካላት ባደረጉት ጉዞ በመጨረሻ በትግራይ ክልል የምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋን አነጋግረዉ ሲመለሱ መሰብሰብና ማንነታቸዉን መወሰን ሕገ መንግስታዊ መብታቸዉ እንደሆነ ጠቁመው፣ ለአካባቢዉ ዞንና ወረዳ እንዲሁም ቀበሌ ማሳወቅ እንዳለባቸዉ ግን ገልጸዉልናል ይላሉ።

ሆኖም የኮሚቴው አባላት ከወረዳዉ አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ ታደሰ ጀምሮ የበታች ሹማንንት የመሰብሰብ መብት እንደነፈጓቸዉ ይናገራሉ።

አቶ ኢሳያስና የወልቃይት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አጄጃዉ አብረሃን ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት ስልካቸዉ ስለማይነሳ አልተሳካም። የወልቃይት ወረዳ የፕሮፓጋንዳ ሃላፊ አቶ አባሆይ ማሙን ግን አግኝተናል።

ትዝታ በላቸዉ ሁለቱን ወገኖች አነጋግራ ተከታዩን አዘጋጅታለች። ሁለት ”የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ” ኮሜቴ አባላት እራሳቸዉን በማስተዋወቅ ይጀምራሉ። የድምጽ ፋይሉን በመጫን ዝርዝሩን ያዳምጡ።

በወልቃይት ህዝብ ማንነቱ ዙሪያ የተጠናቀረ ዝግጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:38:21 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG